የቀን : እረኛ : የሌሊት : ጠባቂ : ቅዱስ : ሚካኤል
#ሰኔ_12_ቀን ቅዱስ ሚካኤል ቅድስት አፎሚያን ከዲያብሎስ መንጋጋ ያስጣለበት እንዲሁም የባሕራንን የሞቱን ጦማር ቀዶ ሠርግ ያደረገበትን እለት ነው ።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ልጆቿን ሰብስባ በዓልን ሰርታ በታላቅ ድምቀት ከዓመት ዓመት ታከብረዋለች ።
መጋቤ ብሉይ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በተአምራቱ ዘወትር እንደሚጠብቀን ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድ እንዲህ እያለ ይመሰክራል ፦
« የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የቀን እረኛ የሌሊት ጠባቂ ክንፎቹ የእሳት የሆነ ዘወትር የሚጠብቀን ቅዱስ ሚካኤል የእውነት የድንኳን ከተማ ነው ። » በማለት ተናግሯል ።
በዚህ መሠረት ድንኳን ከቀን ሐሩር ከሌሊት ቁር እንደሚከለሉበት ሁሉ #ቅዱስ_ሚካኤልም በቃል ኪዳኑም የሚታመኑትን ሁሉ ከምሕረት አልባው ከዲያብሎስ ደባ ከአጋንንት ድብደባ ከዚህ ዓለም ፈተና ያድነናል ይታደገናል ።








