#ዕለታዊ_ዘገባዎች
በሁለት ግንባር በተቀሰቀሰዉ ውጊያ 44ኛ ክፍለ ጦር ድል መቀዳጀቱ ተነገረ።
የአፋብን ጎጃም ጠቅላይ ግዛት ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድረው ከእንጅባራ ቲሊሊ ሰከላ ቀጠና በተቀሰቀሰው አውደውጊያ የአገዛዙ ሀይል ቅስም ሰባሪ የሆነ ሽንፈት አስተናግዷል።
የእሳት ረመጥ ወደ ሆነዉ የ44ኛ ክፍለ ጦር ቀጠና በተንቀሳቀሰዉ የብልፅግና ሎሌ ላይ በተከፈተዉ ዉጊያ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ጣፋጭ የሆነ ድል አስመዝግቧል።
በራያ ግንባር መሸጎ የነበረው የኦህዴድ ዙፋን ጠባቂ በጀግኖቹ የትግራይ ሰራዊት እና የፋኖ ጥምር ሃይሎች (ፅምዶ) በወሰዱት የተቀናጀ መብረቃዊ ጥቃት የጠላት ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል!
በዚህ አንፀባራቂና ታሪካዊ ድል ከ5000 በላይ እግረኛ የጠላት ወታደሮች እጃቸውን ለመስጠት የተገደዱ ሲሆን፣ ስፍር ቁጥር የሌለው ከባድና ቀላል ዘመናዊ የጦር መሣሪያም በፅምዶ ቁጥጥር ስር ውሏል።
በራያ ግንባር በግዳጅ ላይ የሚገኙት የጠላት ብልፅግና ሰራዊት ከስምሪት ቀጠና በመጥፋት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮርን ተቀላቀሉ።
ዛሬ ነሐሴ 07/2018ዓ/ም በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ የጠላት የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 1ኛ ኮር 45ኛ ክፍለጦር 4ኛ ሻምበል አዛዥ እና የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 802ኛ ኮር 49ኛ ክፍለጦር 3ኛ ሻለቃ 2ኛ ሻምበል አባል ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ የ102ኛ ኮርን መቀላቀላቸው ተገልጿለ።
https://youtu.be/NSJrk7zwYnk?si=tkDSq8KHLTotYo_H