Final exam አክስቶኝ ከግቢ ወደ ቤት ስሔድ የኔ እናት ልጄ ከሳብኝ,ጠቆረብኝ ብላ ታዝናለች,በስስት አይን… — AMBO UNIVERSITY WELISO CAMPAUS® — TG.ME

Final exam አክስቶኝ ከግቢ ወደ ቤት ስሔድ የኔ እናት ልጄ ከሳብኝ,ጠቆረብኝ ብላ ታዝናለች,በስስት አይን ታየኛለች, አብራኝ ባለመሆኗ ምን ያሕል እንደተጎዳው ታስባለች ከዛም ባለ በሌለ አቅሟ ጉዳቴን ለመጠገን ትመግበኛለች, ውበቴ እስኪወጣ አስተኝታ ትቀልበኛለች ይሔ ሁሉ ግን ስለ ከሳሁባት እና ስለ ጠቆርኩባት ብቻ ነው። አሰብኩት በሰሞኑ ግርግር የልጃቸውን ሬሳ በሳጥን የተቀበሉ እናቶችን... ሰውነቱን ለመጠገን ይቅርና ልጃቸውን ለመሰናበት እድል ያጡትን, የልጃቸውን የከሳ ሰውነት, የጠቆረ ፊት ለማየት ያልታደሉትን, አሰብኳቸው ምን እንደሚሆኑ ምን እንደሚውጣቸው !! የልጇ ደም እንደ ቀልድ የፈሰሰባት እናት እንዴት እንደምትሆን አስቡት, በማያውቀው ሀገር የቆሰለው, አካል ጉዳተኛ የሆነው ተማሪን እናት አስቡአት, ልጇ ከፎቅ ወድቆ የሞተውን እናት አስቡአት, ከዛን ለትንሽ second ይቺ እናት የኔ እናት ብትሆንስ ብላችሁ አስቡ። ለማሰብ የከበዳችሁ ይመስለኛል ሕሊና ካላቹ። በእናንተ እናት ላይ ሊሆን የማትፈልጉትን በሌላው እናት ላይ ለምን ታደርጋላችሁ?? ሌላዋም እናት ዘጠኝ ወር አምጣ,የእናትነትን ስቃይ ተሰቃይታ ያሳደገች እናት እኮ ናት። እናታችሁን የምትወዱ እባካችሁ ሌላዋም እናት እናት ናትና,ልቧ ተሰብሮ የመረረ ሀዘን ታዝናለች እና ልጇን አትጉዱባት እባካችሁ። ሀዲሱም ቁርዐኑም ቢሆን አንድ ሰው ለራሱ የወደደውን ነገር ለ ወንድሙ እስካላደረገ ድረስ እምነቱ ሙሉ አይሆን፤ ባልንጀራህ ላንተ እንዲያደርግልሕ የምትፈልገውን ነገር ለእሱ ደግሞ አርግለት ነው የሚለው እሱን ማድረግ ቢያቅተን በእኛ እናት ላይ እንዲሆን የማንፈልገውን ነገር በሌላዋ እናት ላይ አናድርግ። እናትሕን ምትወዳት ከሆነ እናት ባለው ተማሪ ላይ ድንጋይ አትወርውር!! አባትም ካለሕ እንደዛው አንተ ብትፈነከት አባትሕ እንደሚያዝን ሁሉ የምትወረውርበት ልጅ አባትም ልቡ ይሰበራል! ከተስማማህበት Share በማድረግ ብዙዎችን እናት እና አባት ከማስለቀስ ተግባር እንዲቆጠቡ አድርግ።

November 21, 2019 9.9K 35