ምንድነው የበሬን ደረት የሚታከከው? ጆሮ ተለጥፎ የሚያዳምጥ ይመስለኛል። ከበሩ ስር ጥላው ተኝቷል። ከውስጥ የሚከናወነውን ለማወቅ ያሰፈሰፈ የሰው ልጅ በሬ ስር ይልከሰከሳል። ከፍቼለት ቢገባ ምንም አዲስ ላያገኝበት ነገር ምን ያንሿክከዋል። ሸከከኝ። አጠገቤ አምጥቼ ያለፈ ምንም አያገኝ። ዋል። ይሄ በሬ ስር የተለጠፈ ጆሮ ባስቀምጠው እንዲሁ ከመፋጠጥ ያለፈ ምንም አያገኝ። ይህን በሬ ላይ የተለጠፈ ጆሮ ጆሮዬን አቁሜ ሳዳምጥ ጣሪያዬ ላይ ያረፉ እርግቦች አናጠቡኝ። ጣሪያዬን በደቃቅ እግሮቻቸው ይራመዱበታል። ጣ..ጣ..የሚል የኮቴያቸው ድምፅ ምናልባት እንደሙዚቃ የማንቸለችለው ጥዑም ዜማ ነው። ብቸኛው መታከሚያዬ ነው። ቀኑ ዓይኖቼ እንደፈጠጡ ጆሮዎቼ እንደቆሙ ይኸው ከሰዓቱን እያጋመሰው ይመስላል። በመስኮቴ ሲገባ የነበረው የፀሀይ ብርሃን የለም። ምናልባት ከአስር አልያም ዘጠኝ ሰዓት ሆኗል። ቀንና ሌሊቱ እንደዚህ በላዬ ላይ ይፈራረቃሉ። ከትላንቴ ያስቀረሁት ለነገዬ ደሞ የማሻግረው ምንም የዚህች ዓለም በረከት የለኝም። እጄ ውስጥ የመዳፌ መሀል ላብ ብቻ እንዲኖር ነው መሻቴ። እጄ ውስጥ የገቡ ነገሮችን ሁሉ ስለቅ ነው የኖርኩት። ወደ ሆዴ ከማስገባው ደረቅ ዳቦ ውጭ ከዚህም ዓለም ከንቱ ንብረት ጣቶቼ እንዲቆነጥጡ አልፈልግም። እጄ ውስጥ ከሚያስፈልገኝ በላይ ምንም ነገር እንዲገኝ አለመዳከሬ ዕረፍት ሰጥቶኛል። ሰው እጁ ውስጥ በያዘው ነገር ክብደት ልክ ነው ሸክሙ ባዶውን የሚኖር ሰላም አለው። ወደ እጁ ለማስገባትም ሆነ የገባውን እንዳይወጣ ከመዳከር ጭንቀት ያርፋል። ራሴን ለማኖር የተራራ ገላ አልቧጥጥም። እግሮቼን የአሸዋ ጥርሶች ላይ አልሞርድም። ትንፋሼ ይቀጥል ዘንድ ያቺ ቁራሽ ደረቅ ዳቦ በቂዬ ነች:: ለማላውቀው ነገዬ የማውቀውን ዛሬዬን አልበድልም። አሁን እጆቻችን ላይ የተደላደሉ የመሰሉን ፀጋዎች የእኛ አለመሆናቸው የሚገባን ጊዜ ይመጣል። ገንዘባችን… ስልጣናችን… ዝናችን በእኛ ላይ የሚሸጋገሩ የዓለም ንብረቶች ናቸው። ለቀጣይ ተረኛ እናስረክባቸዋለን። አሁን አስረነው የወጣነው የእጃችን ሰዓት ምናልባትም በገናዣችን እጅ ይፈታ ይሆናል። 😔 የብልታችን ዙሪያ ፀጉር ሬሳ ሆነን ይላጩት ይሆናል። በቃ ሁሉም ነገር ራሱን ለማስቀጠል የእኛን ህልውና ይጠቀማል። ሁሉም የእኛ አይደለም። የተረኛችን እንጂ! ✨ይቀጥላል✨ #Share #like and #subscribe እያደረጋቹ። 👇Sebscribe YouTube link👇 https://www.youtube.com/@atronose
telegraph.controller.bot/files/1241158414/AgACAgQAAxkBAAKw3GqNTn33WV57K0s7e1xvZzEcc66IAAJYDWsbi6xRU1z6r__RmXZAAQADAgADeQADPQQ
13
2