አትሮኖስ: post #95491 — TG.ME

#አለ_አይደል_አንዳንዴ.. አለ አይደል አንዳንዴ በትዝታ ገመድ የቋጠሩትን ነፍስ ደርቦ መነሳት፤ ሩቅ እያሰቡ የቅርብን ሰው መርሳት፤ . አለ አይደል አንዳንዴ... መንገዴን ተሻግራ አልፋ ለሄደች ሴት ፍቅሬን እንዳትረሳው፤ መስዋዕት ላቀርብላት አጠገቤ ያለች ንፁኋን ሴት ረሳው፤ . መርሳት ብርቅ አይደለም! ማሰብ ብርቅ አይደለም! . ለትዝታ ብላ የተሰዋች ሄዋን ታንጎራጉራለች ፍቅሬ ላይ ተንጋልላ፤ ስለት ታስገባለች 'የትዝታ ስንቁን' የኔ ያርገው ብላ፤ . አንድ ቀን ሕልም አላት ባለትዝታዋን ሆና ለመገኘት የኔን ታማሚ ልብ ለማቁሰል መመኘት . አለ አይደል አንዳንዴ... ፍቅርን የሚመስል ቂም ቋጥሮ ያኖረው ድብቅ ምኞት አለ፤ ሕመም አልጨምርም የሕመሜ ዋሻ ትዝታዬ እያለ፤ . አለ አይደል አንዳንዴ... 🔘ልዑል ሀይሌ🔘

👏11❤5
August 18, 2026 4.2K 1