እናንተዬ ይሄ የAI መዝ 🤯.,,,,,( እኔጃ መዝሙር ማለት ያለብኝ አይመስለኝም ) ለምን እንደሆነ አላውቅም… — Aster Abebe Official — TG.ME

እናንተዬ ይሄ የAI መዝ 🤯.,,,,,( እኔጃ መዝሙር ማለት ያለብኝ አይመስለኝም ) ለምን እንደሆነ አላውቅም አሮን ቀጥቅጦ የሰራውን ጥጃ ይመስለኛል። ያው በእጁ ቀጥቅጦ ሰርቶ ቢሆንም ሙሴ እንዴት እንዲህ ታደርጋለህ ፣ ህዝቡን ታስታለህ ብሎ ሲጠይቀው እንደመለሰው አይነት ዛሬ ላይ እስትንፋስ ከሰጠን ከሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ጋር ያልተነካ ፣ ከህልውናው ጋር ያልተሻሸ በምትኩ የምርም አሮን እንዳለው ወርቁን ወረወርኩት ጥጃ ሆኖ ወጣ እንዳለው አሁንም ጥቅስ ሲያቀብሉት ስብከትም መዝሙርም ከሚወጣው ጋር ይመሳሰልብኛል🫣። እኔ እሱን ሰውዬ ወይስ አቶ AI ወይስ እኔጃ ማን ብዬ ልጥራው ........ በቃ አይጥመኝም። እንደሙሴ እተራራው ላይ ቆይቶ ፣ ሰንብቶ ፣ ተነካክቶ ፣ በቃ ቀረ አይመጣም ፣ ምንአልባትም ሞቶዋል ተብሎ ድንገት ይዘው የወረዱት ከሰሪዋ ጋር ከሰነበተች ምንጭ የተጨለፈ ስለሚሆን ለሁሌም ቢሆን እነሙሴን ፣ እነዳዊትን ፣እነአሳፍን አሁንም ደግሞ እንደነሱ ያሉትን እነ ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶን ፣ እነ ጋሽ ታምራት ሀይሌን ፣ሊሊዬን ፣ላሊዬን ፣ዳጊዬን ፣ዳኒዬ ፣ አዙዬን ፣እነ ቤቲዬን *2 ፣ መስፍኔ፣ ተኬዋ፣ ፀሀይ ዘለቀ፣ አስቴር ተፈራ፣ ፓስተር እንድርያስ ሀዋዝ ፣ እንዳልክዬ፣ ሳሚዬ ፣ ተስፋዬ ጫላ ፣ ኬፊሾ ፣ አውትሽዬ ፣ ዶክተር ደረጀ ከበደ ፣ ተመስገን ማርቆስ ፣ጋሽ ሸዋዬ ዳምጤን፣ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ዘማሪዎችን ..,......... አይ ሲያቀብጠኝ ስም መጥቀስ ጀምሬ መቋጫው ጠፋኝ ከቀደሙት መጥራቴ ነው በኔ ቤት። ያጎደልኩትን እናንተው አግዙኝ ቅዱሳን 🙏🏽 የነሱን ልሰማ ጀመርኩ እንጂ መች ጨረስኩና ? ሁሉ በየአይነቱ አለልኝ። ዘማሪዎችን በሙሉ ብዙ ለምልሙልኝ እያልኩ 😍 AI 😡 “እነርሱም ‘በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን፤ ያ ከግብጽ ያወጣን ሙሴ ምን እንዳገኘው አናውቅም’ አሉኝ። ስለዚህ፣ ‘ማንኛውም ዐይነት የወርቅ ጌጣጌጥ ያለው ሁሉ ያውልቀው’ አልኋቸው፤ ከዚያም ወርቁን ሰጡኝ፤ ወደ እሳቱ ጣልሁት፤ ይህም ጥጃ ወጣ።”” ዘፀአት 32 : 23 - 24 NASV

August 20, 2026 4.5K 17