Aster Abebe Official: post #120 — TG.ME

እንዴት አደራችሁ ቅዱሳን 😍 ያለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ወክ ላደርግ በወጣሁበት መንገድ ላይ ያየሁትን ተክል ፎቶ አንስቼ ትንሽ ልል ፈለኩ። 👇🏽ዛፉ ቀጥ ብሎ ለማደጉ ምክንያት የሁኑት በፐርፕል ቀለም ያከበብኩበት ላይ የተተከሉት ሁለቱ እንጨቶች እና በማደግ ላይ ባለው ዛፍ ላይ ተጠምጥሞ የታሰረው ገመድ እያደገ ያለውን ተክል እንደፈለገ እንዳይንቀሳቀስ ፤ በዛም ምክንያት ተጣሞ እንዳያድግ ትልቅ አስተዋፅዎ ያደረጉ መሆናቸውን እንግዲህ የዛፉ ቀጥ ብሎ ማደግ ምስክር ነው። ዛሬ ላይ በራሳችን ሆነ በልጆቻችን ላይ ምናደርጋት ጥቂት አስተዋፅዎ ነገ ውጤት ስላላት እግዚያብሄር የተሰጠንን ሀላፊነት የምንወጣበትን አቅም እና ፅናት ይሰጠን ዘንድ ፀሎቴ ነው። ጎን እና ጎን የተሸጎጡት እንጨቶች ከጊዜ በዃላ ዛፉ ሲያድግ አቅም የላቸውም። ምክንያቱም ሁለቱን እንጨቶች በቁመት እና በጉልበት እየበለጣቸው ስለሚሄድ። ስለዚህ የዛሬ ፀሎት ፣ የዛሬ ጥቂት ትጋት ፣ የዛሬ ጥቂት ማስገደድ የነገ እድገታቸው ላይ ማሳበቁ ስለማይቀር እየሄዱ እያለ ዛሬ በሚሄዱበት መንገድ መምራት ይሁንልን።

❤156🔥54🙏26🥰12
June 9, 2026 11.9K 29