Aster Abebe Official: post #119 — TG.ME

ኢያሱ 8፤34-35 ልጆቻችን ሲበሉ ፣ሲለብሱ ፣ ተምረው ጥሩ ውጤት ሲያመጡ ፣ስንድር ፣ ሲወልዱ ፤ ሌላም ሌላም ሲሆን ያለንን ደስታ መቼም ወላጅ የሆነ ሁሉ ስለሚያውቀው ይህን ይመስላል ማለት አይጠበቅብኝም። ግን ግን ልጆቼ ቃሉን ሲያነቡት ሳይ ልቤን በደስታ እፍን ነው ሚያደርገኝ። ባለፈው ሳምንት ላገልግሎት ወጥቼ በነበረበት የኔዋ ናኒዬ ትንሽ ጫን ብሎ የባይብል ንባቧን ሚያስቀጥላት ጉልበተኛ ጠፍቶ አላነብም ብላ ለሰባት ቀናት ወደዃላ ቀርታብኝ ነበር። ከርቀት ኮስተር ብዬ ላስቀጥል ብፍጨረጨር ምንም አታመጭም ስትል በእንቢታዋ ፀንታ ቆይታኝ ስመለስ የመሪነቴን ቦታ በክብር ለቃልኛለች። ያው የራሳቸውን ኑሮ ከኔ ተለይተው በራሳቸው እስኪመሩ ድረስ ኢያሱ ያደርግ እንደነበረው ቃሉን ወደዱም ጠሉ ፤ መራራውንም ጣፋጩንም በአመት ጨርሰው የማንበብ ግዴታ አለባቸው። የቤቱ ህግ ነው እንግዲህ ምንም ማድረግ አይቻልም። ይጠቅመናል ብለው በራሳቸው ማንበብ እስኪጀምሩ ይጠቅማችዃል ብዬ ማድረጉን በጌታ ብርታት እቀጥላለው። ሰሞኑን አንድ ነገር ደጋግሜ አስባለው። ለ special kids የሚሰጠው የቴራፒ ፕሮግራም ለውጡን ባንድጊዜ አታዩትም። ያለማቋረጥ በማድረግ ግን ጥሩ ለውጦች ይኖሩታል። ታዲያ የሰው እውቀት በልጆቻችን ላይ ይህን ማድረግ ከቻለ ይህ የእግዚአብሄር ቃል እንዴት የላቀውን ፣ የከበረውን ፣ የሚያስደምመውን አያደርግ ክብር ለቃሉ ይሁን የቴራፒ ብዛት ልጆቻችንን ከሌሎች ልጆች እኩል ለማድረግ የሚታትር ፕሮግራም ነው። ቃሉ ግን ከሰው ሰፈር አይደለም በኩሩን ይመስሉ ዘንድ የሚያስችል አቅም ያለው የፀጋ ቃል ነው። ።።።።።። እና ስጀምር እንዳልኳችሁ ወደዋላ የቀረችበትን አንድ ሳምንት ጠዋት ማታ እያነበበች የቀራት የሁለት ቀን ብቻ ነው። ያልጀመራችሁ ጀምሩ ፤ ያቋረጣችሁ ቀጥሎ ለማለት ያህል

June 7, 2026 11.6K 16