Aster Abebe Official: post #113 — TG.ME

በሉ እንግዲህ .......ወላጆች በሙሉ ልጆቻችንን ሰብስበን መፅሀፍ ቅዱስን ልናነብላቸው ግዴታ እንዳለብን የኢያሱ መፅሀፍ ገላግሎናል። አራስ የለ ፣ ህፃን የለ ፣ ሸስማግሌ ፣ ወጣት ፣ ታዳጊ ለሁሉ ነው ሚለው። ፊደል ይቁጠር፤ ይደግ ምናም አይሰራም። ካደጉ በዃላ አንብብ አታንብብ ትግል ከመግጠም በስድስት ወራቸው በነጭ ሽሮ በእጃችን ፍጭት አድርገን ገና ስሙ ሳይገባቸው እንደምናሰለጥናቸው እንጀራ በወጥ የመፅሀፍ ቅዱሱም ፍቅር ገና ከሆድ እንደወጡ ከተቻለ ደግሞ እንደአንዳንድ የእምነት ተቋማት በሆድ ሳሉ ሊነበብላቸው ይህ የቃሉ ትእዛዝ ነው። አሁን ጀምሩ 📖 ታዲያ መምረጥ የለም ✨ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ✨

January 24, 2026 23.2K 17
በሉ እንግዲህ .......ወላጆች በሙሉ ልጆቻችንን ሰብስበን መፅሀፍ ቅዱስን ልናነብላቸው ግዴታ እንዳለብን… — Aster Abebe Official — TG.ME