ማልጄ እነሳለው የሱስን ላከብር ተለማምጃለው እኔስ በአምልኮ ድል በገናው ይደርደር ምስጋናው ይወራ እጁ ትመጣለች አሁን ድንቅን ልትሰራ ይነሳለት እልልታ ይውጣ እንጂ ወደላይ ሸለቆ ውሃ ይሞላል ደመናም ባይታይ ይሄማ በእግዛብሄር ሀይል እጅጉን ቀላል ነው ላሰማ የድል ዜማ ብቻ እንዲ ላምልከው ፩) ብቻ ላግኝ እንጂ በፊቱ ሞገስ የሱስ ይቀበለኝ ስሙን ስወድስ በምስጋና ጩህት በዜማ በአምልኮ አይቆምም ይፈርሳል ግንቡ የእያሪኮ እጅግ ታላቅ ድምፅ ብዙ ብዙ ምስጋና ይቀበል የኛ አምላክ እርሱ ትልቅ ነውና በገናውም ይደርደር ከበሮውም ይመታ ይውጣ ወድዙፋኑ የምስጋናችን ሽታ ይናወጣል የወህኒው መሰረት በዝማሬ በአምልኮ ጉልበት የሁሉንም እስራት ይፈታል በጠላቶቹ ላይ ይበረታል እየሱስ ይመጣል በምስጋና ሲጠራ ሲታወጅ ትልቅ ሀይሉ የሱ ዝና ሲወራ ሸክምን ሊያራግፍ ቀንበርን ሊሰብር ሊፈውስ ሊምር አለ ከእኛ ጋር ስሙ ሲጠራ በክብር ገኖ ሀይሉ ይገለጣል የበላይ ሆኖ ፪) ይዘመር ምስጋናው ይጀመር ዝማሬ ይህነው መዋጊያዬ ይህ ነው ድብቅ ጦሬ ታዞበታል ጠላት የበትር ድብደባ እኔ ዘምራለው ፍፁም ያጣል መግቢያ ሲለቀቅ ምስጋናው በጠላት ጆሮ ላይ እየሱስ ይነሳል ይከፈታል ሰማይ ፫) ይዤ መጥቻለው በልቤ ደስታ የምስጋናን ነዶ ለትልቁ ጌታ ይቅጣለት ወደላይ ወደማደሪያው የእርሱ ልቆ መታይ ለኔ ክብሬ ነው ማልጄ እነሳለው...
ማልጄ እነሳለው የሱስን ላከብር ተለማምጃለው እኔስ በአምልኮ ድል በገናው ይደርደር ምስጋናው ይወራ እጁ… — ደስ 💥ያለው_ይዘምር 😁] — TG.ME
August 4, 2025 3.2K 2 35