በAi የተሰራ ጥናት (Academic Research) በሩቁ ይታወቃል። በመሆኑም በሰው የተጻፈ አስመስሎ ማስተካከል (humanize ማድረግ) የብዙ ሰው ፈተና ነው:: የመጀመሪያው ችግር በሰው የተጻፈ ለማስመሰል ለAi የሚሰጠው ትእዛዝ (Prompt) ነው። ምክንያቱም በትክክል ካልታዘዘ በትክክል አያስተካክልም። ሁለተኛው ችግር ደግሞ በሰው የተጻፈ ለማስመሰል የሚያስችል Ai መምረጡ ላይ ነው።
በመሆኑም አንዳአንዶች በጠየቃችሁኝ መሰረት በሰው የተጻፈ ለማስመሰል መጠቀም የምትችሉት ትዕዛዝ (Prompt) ከታች ተያይዟል።
ትዕዛዙን መጠቀም የምትችሉባቸው የተለያዩ አማራጮች አሉ። ለዚሁ ተብለው የተሰሩ "humanizer" ድረ-ገጾች እና Ai ዮችም አሉ። ይሁንና እነዚህ "humanizer" የሚባሉት ድረ-ገጾች እና Ai ከሚሰጡት ዝቅተኛ ጥራት ያለው ጽሑፍ ባሻገር በዋናነት የተሰሩት የAI መፈለጊያዎችን (detectors) ለማታለል ስለሆነ አስተማማኝ አይደሉም፤ ደግሞም ከሥነ-ምግባር አኳያ አጠራጣሪ ናቸው። (እንድትጠቀሙባቸው አልመክርም)
ስለሆነም የተሻሉ ተብለው ከሚታወቁት አስተማማኝ Ai ዮች Claude እና ChatGPT ይጠቀሳሉ። በተለይም Claude 3.5/3.7 Sonnet ረጅም ሰነዶችን (ጥናቶችን ) ለማስተካከል በጣም ተመራጭ ነው።
ChatGPT Plus / GPT-4o ደግሞ ሁለገብ እና መመሪያን አጥብቆ በመከተል ውስብስብ ጉዳዮችን በከፍተኛ ደረጃ የሚያስተካክል እንደሆነ ተመስክሮለታል።
በመረጃ የተደገፈ ጽሑፍ ከምንጮች ጋር በማመሳከር ደግሞ Perplexity Pro አንደኛ ነው። ሀሰተኛ መረጃ የመፍጠርም ሆነ የማሳለፍ ዕድሉ አነስተኛ ነው። (ጥናት ለመስራትም ጥሩ አማራጭ ነው።)
የዓረፍተ ነገሮች ውበት እና አጻጻፍ ማስተካከያ QuillBot ወይም Wordtune ድረ ገጾችም አማራጭ ይሆናሉ። ይሁንና ሙሉ ጥናቱን ሳይሆን በምዕራፍ - በምዕራፍ እያቀናነሱ መጫን የተሻለ ውጤት ያስገኛል።
በበተጨማሪም የአካዳሚክ ጽሑፎችን በሰው የተጻፉ ለማስመሰል Paperpal እና Jenni AI መጠቀም ይቻላል። የሳይንሳዊ ጽሑፎች ቋንቋ በጥራት ይቀይራል፤ ይዘቱ የሮቦት እንዳይመስል ያደርጋል።
---
የእኔ ምክር
የጥናት ጽሁፉን Claude 3.7 Sonnet ወይም ChatGPT Plus ላይ#Upload አድርጎ ያያዝኩት ትዕዛዝ (humanization prompt) መጠቀም ይመረጣል።
#ማሳሰቢያ :-
1. ምንም ያህል በየትኛውም Ai ሰው የጻፈው እንዲመስል ቢደረግም ከ70% በላይ ውጤታማ የሚሆነው ከላይ የተጠቀሱትን የተሻሉ አማራጮች ከተጠቀሙ በኋላ በማንዋል (በራስ) ማስተካከል ሲቻል እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል።
2. አንድ ጥናት መጀመሪያ በፕሮፖዛል ደረጃ Humanize መደረግ አለበት። ከታች ያለው ለዚሁ የተዘጋጀ ነው። ላለቀለት ጥናት እንዲሆን መቀየር ከፈለጋችሁ ChatGPT በመጠቀም ቀይሩት
1August 16, 2026 334 9