Aleph Academy ,Hawassa: post #335 — TG.ME

ዛሬ ማለት ታህሳስ 12 (Dec 21)ፀሐይ ከጠዋቱ 12:35 ላይ ትወጣለች ! የኢትዮጵያ ቀደምት አባቶች ያረጋገጡት ሃቅ ! #Ethiopia | በስነ ፈለክ ስነ ክዋክብት ቀደምት የኢትዮጵያ ምርምሮች በማጥናት የሚታወቀው ዶክተር ሮዳስ በነገው እለት ታህሳስ 12 በመላው አለም ቀኑ አጭርና ለሊቱ ረጂም እንደሚሆን ገለፀ ። ዶክተር ሮዳስ ክስተቱን በተመለከተ በቪዲዮ ባቀረበው ዝግጂት እንደገለፀው ። ፀሐይ በአመት ዉስጥ በሰማያዊ ሉል በምታደርገው ጉዞ 4 ልዩ ክስተቶች ይፈጠራሉ ። በዚህም ምክንያት የቀንና ለሊት የሰአት መለያየት ይፈጠራል ። ከእነዚህም አንዱ የሆነው የታህሳስ ጀምበር ይጠቀሳል ። በመሆኑም ታህሳስ 12 ፀሐይ ከጠዋቱ 12:35 ላይ የምትወጣ ሲሆን 12:11 ።ደቂቃ ላይ ወደጀንበሯ ትጠልቃለች ። ብሏል ዶክተር ጉዳዩን እንዲህ እንዲህ በሰፊዉ አብራርቶታል ። "ታህሳስ 12 ፀሀይ በፍኖተ ፀሐይ ወይም በፀሐይ ጎዳና ወደ ደቡብ የምታደርገውን ጉዞ የምታቆምበት እለት ነዉ ። እለቱ በሰሜኑ ንፍቀክበብ የክረምት መጀመርና በረዶና ዝናብ የሚጀምርበት ቀን ሲሆን ቀኑ አጭርና ለሊቱ ረጂም ይሆናል ። ይህ እለት በተለይም በሰሜኑ ንፍቀክበብ ሰዓት አቆጣጠር ስለሚያዛቤ ፈረንጆቹ ሰአቱን ለማመጣጠን ማስተካከያ ያደርጉበታል ። በአንፃሩ ደግሞ በደቡብ ንፍቀክበብ ለአንድ ቀን ሙሉ የማትወጣበት ሙሉ ቀኑ በጨለማ የሚዋጥበት ሁኖ ይዉላል ። በእርግጥ እኛ የምድር ወገብ አካባቢ ስለሆንን ልዩነት ብዙም አንረዳዉም በወደ አዉሮጳ አካባቢ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ድቅድቅ ጨለማ ይሆናል ከእኛ ግን 12/30 ድረስ ሊቆይ ይችላል ይህም የገና ጀምበር ተብሎ ይጠራል ። ትርጉሙም የአለም ገናናው ንጉሥ እየሱስ ክርስቶስ ዉልደት ለአለም ሁሉ ሁሉ የከፈተው የብርሃን በርን ያመለክታል ።" ሲል ገልጿል ። በተመሳሳይ አጠቃላይ ስለምድሪቱና ኢትዮጵያዊያን ጠበብት የገለፀው ዶክተር ስለ ኢትዮጵያ ፊደላት ይህን ብሏል ። በኢትዮጵያ ፊደለ ቀመር ከያዛቸው ሚስጥራት መካከል አንዱ "የብርሃን ቀመር " የተፈጥሮ የወቅቶች ኡደት እንደሆ የገለፀው ዶክተር ሮዳስ አባቶቻችን የፀሀይን መዞርን በማጥናት በምድር ወገብ እኩል የምትሆንበትን ተመራምረው የቀኑና የሌሊት እኩል 12 የሚሆኑበትን የመስከረምና የመጋቢት እኩሌን አሜስጥረዋል። የግዕዙን ፊደላችን ካየነዉ ወደታች 26 ወደጎን 7 ሲሆን 26×7 =182 ይመጣል በዚህም ቀኑና ለሊቱ እኩል ይሆናል ። ፌደላቶቻችን ጥልቅና ረቂቅ ሚስጥር ያለዉ ሲሆን ወደጎን ሰባቱ ብሩሃን ደማቅ አካላትን የሚወክሉ ናቸው ሀ ፀሐይን ፣ ሁ= ጨረቃን ፣ሂ= ማርስን ሃ ሜርኩሪን ሄ =ጁፒተር ፣ህ ቬኑስ፣ ሆ =ሳተርንን ይወክላሉ ። እለታትን ስያሜ ጨምሮ በዓላትን በቀመርና በሚስጥር ነዉ በአቡሸሀር የተረቀቀው ለምሳሌ እኛ አዲስአመት መስከረም 1 ፀሐይ በምድር መካከል ስለምትዉል ቀኑና ለሊቱም እኩል ስለሆነ ነዉ ኢትዮጵያዊያን ሊቃውንት ከዘመን ወደዘመን የምንሸጋገርበት ያደረጉት በማለት ከሳይንስና ከኢትዮጵያዊ ጥንት ጥበብ በማጣቀስ አስረድቷል ።

👍9
December 21, 2025 2.2K 1