የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአርክቴክቸር ተማሪ በPUBG MOBILE AFRICA Rising Designer Season…

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአርክቴክቸር ተማሪ በPUBG MOBILE AFRICA Rising Designer Season 2 አሸናፊ ሆነ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአርክቴክቸር ተማሪ የሆነው ተማሪ ቅዱስ ተስፋሁን PUBG MOBILE AFRICA ባዘጋጀው Rising Designer Season 2 የዲዛይን ውድድር በዳኞች ምርጫ እና በሕዝብ ድምፅ ሁለት የአሸናፊነት ማዕረጎችን በማግኘት የዩኒቨርሲቲውን ስም በአህጉራዊ ደረጃ አስጠርቷል።

Rising Designer Season 2 በአፍሪካ ለሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የተዘጋጀ የዲዛይን ውድድር ሲሆን፣ ወጣት ዲዛይነሮች የፈጠራ ችሎታቸውን እንዲያሳዩ፣ ከሌሎች ጋር እንዲወዳደሩ እና በተግባራዊ የዲዛይን ፕሮጀክቶች ላይ የመሥራት ልምድ እንዲያገኙ ዕድል ለመፍጠር ያለመ ነው።
ተማሪ ቅዱስ ተስፋሁን ከ85 በላይ የዲዛይን ሥራዎች መካከል ወደ ምርጥ 10 (Top 10) ተወዳዳሪዎች ደረጃ ማለፍ ከመቻሉም በላይ በዳኞች ምርጫ ከምርጥ 10 ውስጥ ወደ ፍጻሜው ውድድር (Final) ከተሸጋገሩት አምስት ተወዳዳሪዎች መካከል ተካቶ ነበር። ተማሪ ቅዱስ በዳኞች ምርጫ እና በሕዝብ ድምፅ የሚሰጡትን ሁለቱንም የአሸናፊነት ማዕረጎች በማግኘት የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል።
ተማሪ ቅዱስ ውድድሩን ማሸነፉን ተከትሎ በደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው LOUDRABBITS ስቱዲዮ ጋር የሚከናወን የክፍያ የሥራ ልምምድ (Paid Internship) ዕድልና የዕውቅና ሽልማት (Recognition) እንደሚያገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ተማሪ ቅዱስ የውድድሩ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ በሰጠው አስተያየት ድሉ የግል ስኬት ብቻ ሳይሆን የሚማርበትን ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲና የአርክቴክቸር ዲፓርትመንትን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ያስቻለ መሆኑን ገልፆ የዩኒቨርሲቲውን ስም በማስጠራቱ ከፍተኛ ኩራትና ደስታ እንደተሰማው አስረድቷል
👏10😁3❤2
November 20, 2026 956 3