በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የ"ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" ማኅበር አባላትና የትምህርቱ ተካፋዮች በሙሉ፦ የእግዚአብሔር ሰላም ፍቅርና ጥበቃ በያላችሁበት ይብዛላችሁ፡፡ ማኅበራችን "ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" በዚህ ዓመት የክረምት ወቅት ለወልድያ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችና ምዕመናን ባዘጋጀው ልዩ የመንፈሳዊ ትምህርት መርሐ ግብር መሠረት ትምህርታችን የሆነውን "የነገረ ድኅነት" ትምህርት በሰፊው እየተማርን እንገኛለን።
ይህ እጃችሁ ላይ የደረሰው የነገረ ድኅነት 3ተኛው (Handout) በክፍል ውስጥ የተማርነውን ይዘት በቤታችሁ ሆናችሁ በሰፊው እንድታነቡት እንድታጠናውና ለሕይወታችሁ ስንቅ እንድታደርጉት ይበልጥ በሚያመች መልክ ተደራጅቶ የተዘጋጀ የፒዲኤፍ (PDF) ሰነድ ነው።
በዚህ ክፍል ሦስት ሰነድ ውስጥ፦
የሰዎች ውድቀት፦ አዳምና ሔዋን በሕግ መተላለፋቸው ያስከተለውን መዘዝ
ጥንተ አብሶ እና ምልዕተ ኃጢአት፦ የቃሉን ምስጢራዊና መጽሐፋዊ ትርጉም፣
የባሕርይ መጎስቆልና ሞት፦ የሰው ልጅ ከኃጢአት በኋላ ያጣውን ክብርና የደረሰበትን የባሕርይ ውድቀት ኃጢአት በዘር ይተላለፋልን? የሚለውን ጥያቄ ከነቢያትና ከአበው ትምህርት አንጻር
አዳኝ ማግኘት አለመቻሉን፦ ነቢያት፣ መላእክት፣ የመሥዋዕተ ኦሪትና የኦሪት ሕግ ሰውን ሙሉ በሙሉ ማዳን ያልቻሉበትን ምክንያቶች ለአቀራረብ በሚመችና ግልጽ በሆነ ቋንቋ በዝርዝር በዚህ ሃንዳውት አስቀምጠናል።
ይህ መነሻ አዳም ከምን ዓይነት የጸጋ ከፍታ ላይ እንደወደቀና የእግዚአብሔር አምላክ የማዳን ሥራ ምን ያህል አስፈላጊና ድንቅ እንደሆነ ለአእምሯችን ፍጹም መረዳትን ይሰጠናል።
እናንተም ይህንን ሰነድ ከግሩፑ አውርዳችሁ (Download አድርጋችሁ) https://t.me/Stpoulos በስልካችሁ ላይ ዝም ብሎ እንዲቀመጥ ሳይሆን በጸሎት መንፈስ ሆናችሁ በደንብ እንድታነቡትና እንድታጠኑት በቅዱስ እግዚአብሔር ስም አደራ ማለት እወዳለሁ።
የቀደሙት አባቶቻችንና ቅዱሳን ሐዋርያት የተጋደሉለትን ደማቸውን ያፈሰሱለትንና የጻፉልንን እውነተኛውን የመዳን እውቀት (የነገረ ድኅነት ምስጢር) አውቀን በእምነት እንድንጸና እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ይደልውልን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
አቤል ተፈራ በላይ
ሐምሌ 30 2018 ዓ/ም




