#ቴዎድሮስ_ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
#ታየኝ
🎹🥁🥁🎹
🥁🎷🎷🥁
ለአይኔ አበሰረች አዲስ ጀምበር
ከፍታው ስትገባ የልቤን በር
ሳየው አንድአይነት የነበረ
ሁሉም ወደ አዲስ ተቀየረ
እውነት እናውራ ከተባለ
ለኔስ እንዳንቺ አንድም የለ
በዓለም ያልታየ ጥበብ ነክሮ
ልዩ አደረገሽ አሳምሮ
🎷🥁🥁🎷
እስከዛሬ
ማድነቅ የምናውቅ መስሎን ኖረን
መልክሽ ውበትን አስተማረን
ፈዘው ማየት
ገና ጀመሩ ሰው ዓይኖቹ
ቁንጅናን ባንቺ ሳይሰለቹ
🎵
እኛም ብለናል ገርሞን በጣም
ሰው አምሮ ከሰው እንዲህ አይወጣም
🎷
ነፍስሽማ
ቆርጦ የሄደን ነው አስመላሽ
ቀአንቺ ሚጨክን የለም ጭራሽ
ዓለም ያኔ
አይኔን አድርሳው ለማልቀስ
ፈገግ አረግሺኝ እንደአዲስ
🎵
ከፀሀይ ከዝናብ ከለላዬ
ውብ የእናቴ አምሳል ነሽ ጥላዬ
🎷🥁🥁🎷
ቁምነገርሽን አይቶ
የማያደንቅ የለም
አልተገኘም ላንቺ
አቻሽ በዚህ ዓለም
የጫወታሽ ለዛ
እየነሳው አቅም
ሰው ያለውን ሚስጥር
ካንቺ አይደብቅም
🎶
ድንገት ከሰው መሀል ወጥቶ
ላወራሽ ቀኑ ቀንቶ
መቼም አይጠግብሽ ሰምቶ
አቤት ካንቺ ጋር ጨዋታ
አቤት ካንቺ ጋር ጨዋታ
የማይረሳ ትዝታ
አቤት ካንቺ ጋር ጨዋታ
ሲያምር ካንቺ ጋር ጨዋታ
የማይረሳ ትዝታ
የማይረሳ ትዝታ
🎶
ለአንዴ ቀርቦ ያወራሽ ሰው
የለም የሚመልሰው
ታየኝ ሲሆን ሱሰኛ
መሽቶ ሌትም አይተኛ
ለአንዴ ቀርቦ ያወራሽ ሰው
የለም የሚመልሰው
ታየኝ ሲሆን ሱሰኛ
መሽቶ ሌትም አይተኛ
🎷
ታየኝ ታየኝ ታየኝ
🎷🥁🥁🎷
ታየኝ
ታየኝ ሲሆን ሱሰኛ
መሽቶ
መሽቶ ሌትም አይተኛ
ታየኝ
ታየኝ ሲሆን ሱሰኛ
መሽቶ
መሽቶ ሌትም አይተኛ
ኦሆ. . . ኦሆ. . .
🎷🥁
ለአንዴ ቀርቦ ያወራሽ ሰው
የለም የሚመልሰው
ታየኝ ሲሆን ሱሰኛ
መሽቶ ሌትም አይተኛ
ለአንዴ ቀርቦ ያወራሽ ሰው
የለም የሚመልሰው
ታየኝ ሲሆን ሱሰኛ
መሽቶ ሌትም አይተኛ
🟩🟨🟥
@J_Sancho255


