መቼም የማይረሳኝ ገጠመኝ።
1997 መርካቶ ላይ አፈሳ ተጧጡፎ
ወጣት የሆነ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም ለማምለጥ ጀለቢያ ይለብስ ነበር።
እና ሀለፎም የሚባል የሰፈራችን ልጅ ጀለቢያ ይገደግድና ወደ በርበሬ በረንዳ ይሄዳል።
በትልቅ ካቻማሌ ወጣቱ ሲጫን ጀለቢያ ለበስኩ ብሎ እየተንቀባረረ ሲንጎማለል
አንድ ወታደር “አንተ ና ወደዚህ፣ግባ ወደ መኪናው”
ሲለው “አረ ሙስሊም ነኝ ከመስጂድ ነው እየመጣሁ ያለሁት ጀለቢያ ለብሼ አታየኝም?” ሲለው
ወታደሩ ምን ቢል አሪፍ ነው።
“ዝም ብለህ ግባ ለዱአ ታስፈልገናለህ”
አረ ኡኡኡኡኡ😂😂😂😂
መልካም ቅዳሜ


