WENDE TUTORIAL: post #4607 — TG.ME

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ፕሮግራሞቹን የሚያስተዋውቅበት የ2019(2026/27) ትምህርት ዘመን የመረጃ ሳምንት» ተጀመረ::
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ኮሌጆቹና የትምህርት ክፍሎቹ የሚሰጧቸውን የትምህርት ፕሮግራሞች ለተማሪዎችና ለተማሪ ወላጆች የሚያስተዋውቅበት «የመረጃ ሳምንት» ዛሬ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በይፋ ተከፍቷል::
በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ሲድስት ኪሎ በሚገኘው ፎረም ሕንፃ እስከ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ በሚቆየው በዚህ መርሃ-ግብር፤ የሚከተሉት ዋና ዋና መረጃዎችና አገልግሎቶች ለጎብኚዎች ይቀርባሉ።
• የቅድመ-ምረቃና የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ መስፈርቶች እና የማመልከቻ ሂደቶች፤
• የመጀመሪያ ዲግሪ የመግቢያ ፈተና አስፈላጊ መረጃዎች፤
• የመንግስት፣ የግል እና የፕሬዝዳንታዊ ስኮላርሺፕ አማራጮች ማብራሪያ፤
• ከተማሪዎች ምደባ እና ከትምህርት ክፍሎች አመዳደብ ጋር የተያያዙ ዝርዝሮች እና ሌሎችም መረጃዎች ይቀርባሉ።
ይህ መርሃ-ግብር በተለይም ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ላጠናቀቁ ተማሪዎች እና የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ለመቀጠል ለሚፈልጉ አመልካቾች፤ ስለ ዩኒቨርሲቲው ፕሮግራሞች ቅድመ-ግንዛቤ እንዲጨብጡ ለማስቻል የተዘጋጀ ነው።በተጨማሪም ከየኮሌጆቹ ከተወከሉ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር በቀጥታ በመገናኘት የገፅ-ለገፅ ማብራሪያና ምክር ማግኘት ይችላሉ።
<<አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይማሩ፤ ሕልምዎን ያሳኩ!»

@AAU_EXAM_COLLECTION
❤7
August 15, 2026 1.6K