በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2019 ዓ.ም ለቅድመ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2018 ዓ.ም ለቅድመ ምረቃ ትምህርት በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሽፕ እና በግል ከፍለዉ ለሚማሩ እንዲሁም በማታ በተከታታይ መርሃ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
በዚህም መሠረት በዩኒቨርሲቲዉ ድረ ገጾች (https://www.aau.edu.et ወይም https://admission.aau.edu.et) ላይ የተመለከቱትን ዝርዝር የማመልከቻ መስፈርቶች በማሟላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
የመመዝገቢያ ቀናት ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ
ማመልከት የሚችሉት የ12ኛ መልቀቂያ ፈተና በ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም ወስደው የዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ነጥብ ያላቸው እንዲሁም ለተከታታይ መርሀ-ግብር Diploma +COC4 ያላቸዉ
የዩኒቨርሲቲዉ የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀናት ከጳጉሜ 2 -4 2018 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን::
ተጨማሪ መረጃ በዪኒቨርሲቱዉ ድረ-ገፅ https://www.aau.edu.et t.me/aauGAT እንዲሁም በተለያየ t.me/AAU_Official የቴሌግራም ቻናሎች እንድትከተሉ እናሳዉቃለን::
አ.አ.ዩ ሬጅስትራር
@UATtutorialOfficial
11August 24, 2026 2.6K 1 66