ልብህን አታድክም...🤌 ባለፈው ነገር በመጸጸት ልብህን አታድክም፤ ገና ስላልደረሰውም ነገር በመፍራት… — ✨የረሱል (ሶ.ዐ.ወ) መንገድ✨ — TG.ME

🫀 ልብህን አታድክም...🤌

ባለፈው ነገር በመጸጸት ልብህን አታድክም፤ ገና ስላልደረሰውም ነገር በመፍራት አትጨነቅ። ሁሉም ነገር አላህ በወሰነለት ጊዜ ይደርሳል።

መልካም ሥራን ትንሽ ቢሆን አትናቀው፤ መንገዱም ቢረዝም ታገሥ። አላህ በቅን ልብ የተሠራን ሥራ፣ ወደ እርሱ የፈሰሰችን እንባ፣ ከያቂን ልብ የወጣችን ዱዓ ፈጽሞ አያባክንም።

የተጻፈልህ ነገር በተሻለው ጊዜ ይመጣል፤ ያልተጻፈልህ ደግሞ ከአንተ መራቁ አሁን የማታየው የአላህ ረህማ ሊሆን ይችላል።

ስለዚህ በአላህ ተመካ፣ ስለ እርሱም መልካም ግምት ይኑርህ። በተረጋጋ ልብ መንገድህን ቀጥል፤ ከችግር ጋር እፎይታ አለ፣ ከእያንዳንዱም ጭንቀት በኋላ ፈረጅ አለ።
👍4😢2😭2
August 24, 2026 505 2