Networking | «በካምፓስ ውስጥ GPA ብቻውን በቂ አይደለም» አብዛኛው ተማሪ ትኩረቱን 100% ውጤት… — Temari News — TG.ME

🎓 #Networking | «በካምፓስ ውስጥ GPA ብቻውን በቂ አይደለም» አብዛኛው ተማሪ ትኩረቱን 100% ውጤት (GPA) ላይ ብቻ ያደርጋል። ነገር ግን ከምረቃ በኋላ በሩን የሚከፍትልዎ ያመጡት ውጤት ብቻ ሳይሆን «ማንን ያውቃሉ? ማን እርስዎን ያውቃል?» የሚለው ማህበራዊ ግንኙነት (Network) ነው፦ ❌ ተማሪዎች የሚሰሩት ስህተት በክፍል ውስጥ ገለልተኛ ሆኖ መማር እና ከክፍል ውጭ ካሉ እንቅስቃሴዎች መራቅ። የምረቃ እለት ከፍተኛ ውጤት ይዘው ነገር ግን አንድም የስራ ማጣቀሻ (Reference) ወይም እድል የሚጠቁም ሰው አጥተው የሚቸገሩ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ አይደለም። 💡 በግቢ ውስጥ ጠንካራ Network ለመገንባት 3 መንገዶች፦ ✅ ከመምህራን ጋር አዎንታዊ ግንኙነት ፍጠሩ፦ በክፍል ውስጥ ጥያቄ በመጠየቅ፣ ቢሮአቸው በመሄድ ስለ ትምህርቱ ከተጠበቀው በላይ ፍላጎት ማሳየት። በኋላ ለስራ ወይም ለስኮላርሺፕ የድጋፍ ደብዳቤ (Recommendation Letter) ሲያስፈልግዎት የመጀመሪያ ደጋፊዎችዎ እነሱ ናቸው። ✅ በተማሪዎች ክለቦች (Clubs & Associations) ተሳተፉ፦ በDebate፣ Technology፣ ወይም በበጎ አድራጎት ክለቦች ውስጥ መሳተፍ አመራርነትንና ተግባቦትን ያስተምራል። ✅ ከSeniors ጋር ተቀረቡ፦ የትኞቹ አስተማሪዎች ከባድ እንደሆኑ፣ የትኞቹ ኮርሶች ትኩረት እንደሚፈልጉ እና የፈተና አቀራረቦችን አስቀድመው የሚያውቁት እነሱ ናቸው። 📚ለትምህርት መፅሐፍት 💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes 📣ለትምህርታዊ መረጃዎች 💻 @TemariNews 💻 @TemariNews

September 8, 2026 9.6K 1 33