11ኛ ወይም 12ኛ ክፍል ላይ ያላችሁ… ማትሪክ ተፈትናችሁ ያለፋችሁም ሆነ ያላለፋችሁ… የFreshman ተማሪዎች ወይም ከዩኒቨርሲቲ የተመረቃችሁ —ጉዟችሁን የሚቀይረው የሚደርሳችሁ መረጃ ጥራት ብቻ ነው።
Apex Ethiopia የተቋቋመው ይህን ግራ መጋባት ለማስቀረት ነው፦
100% የተረጋገጠ መረጃ፦ ማንኛውም የስኮላርሺፕ፣ የሥራ እና የኢንተርንሺፕ መረጃ ከOfficial ምንጩ ሳይረጋገጥ በፍጹም አይወጣም።
እውነተኛ ልምድ፦ በአሁኑ ወቅት በ NYU ፣ Yale እና Berea College ከሚማሩ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ቀጥተኛ ተሞክሮ ድጋፍ ታገኛላችሁ።
ሙሉ ታማኝነት፦ ግምት የለም፤ ያልተረጋገጠ ነገር ካለ "አልተረጋገጠም" እንላለን፤ ስህተት ከተፈጠረ ደግሞ በግልጽ አርመን እናሳውቃለን።
አቅሙ ካላችሁ፤ የሚጎድለው ታማኙና እውነተኛው መስመር ብቻ ነው። የወደፊት ጉዟችሁን በጫጫታ ሳይሆን በተረጋገጠ እውነት ላይ መስርታችሁ በማቀድ እንደ USA, Turkey, South Korea, China, Italy ባሉ ሃገራት ወደፊታችሁን በስኬት መጀመር ትችላላችሁ።




