#StudentReality | የኦንላይን Gurus እውነታ እና ለተማሪዎች የሚሆን መፍትሔበየሶሻል ሚዲያው «ትምህርት አያስፈልግም፣ የኔን ኮርስ ገዝተህ በአንድ ወር ሀብታም ሁን» የሚሉ ሰዎች ተበራክተዋል። ይህ ነገር የብዙ ተማሪዎችን ትኩረት እየወሰደ ይገኛል። ማወቅ ያለብዎ 3 እውነታዎች፦ የሽያጭ ስልታቸው ነው፦ አብዛኞቹ Gurus ገንዘብ የሚያገኙት ከሚሰሩት ስራ ሳይሆን «እንዴት ሀብታም መሆን ይቻላል» የሚል ኮርስ ለተማሪዎች በመሸጥ ነው። ስታስቡት ራሱ ያን ያህል ብር የሚያገኙ ከሆኑ ለምን 24 ሰዓት ኮርስ ስለመሸጥ ቪድዮ ሲሰሩ ይውላሉ። አቋራጭ መንገድ የለም፦ በኢንተርኔትም ቢሆን እውነተኛ ገንዘብ ለማግኘት ወራት ወይም ዓመታት የሚወስድ ከባድ ስራና ልምድ ይጠይቃል። መሰረቱ ይጎድላል፦ ያለ ምንም እውቀትና ትምህርት አቋራጭ ፍለጋ መሄድ መጨረሻው ለኪሳራና ለተስፋ መቁረጥ ይዳርጋል። ለተማሪዎች የሚሆን ትክክለኛው መንገድ፦ ትምህርትዎን አያቋርጡ፦ መደበኛ ትምህርት አእምሮዎን የማሰሪያ፣ የማሰብ እና የመጨረስ አቅምዎን ይገነባል። ተግባራዊ ክህሎት ይማሩ፦ በትምህርትዎ ጎን ለጎን እውነተኛ ገበያ ያላቸውን የቴክኖሎጂ ክህሎቶች (እንደ Coding, Graphic Design, Video Editing, Digital Marketing) በነፃ ከዩቲዩብ ይማሩ። ጊዜ ይስጡት፦ በአንድ ጀምበር ሀብታም የሚያደርግ ህልም ውስጥ ከመግባት ይልቅ በየቀኑ 1 ሰዓት አዲስ ነገር በመማር እውነተኛ እውቀት ላይ ኢንቨስት ያድርጉ። ይህ መረጃ ለጓደኞችዎ እንዲደርስ Share ያድርጉ!ለተማሪዎች በተማሪዎች@TemariNews@TemariNewst.me/TemariNews/8307Translate288531September 2, 2026 4.9K 12