The Christian News: post #4707 — TG.ME

#ሰው ግን ምን ያክል በቀለኛ ሊሆን ይችላል ? የበቀል መጨረሻውስ ምን ይሁን ?

የፓስተር ጻድቁ አብዶ "በቀል በቀለኛውን ያጠፋል" የተሰኘው መጽሀፍ በአፋን ኦሮምኛ እና በትግረኛ እየመጣ ነው። በእንግሊዘኛ የተዘጋጀው መጽሀፍ አሁን ደግሞ በሁለት ቋንቋዎች በዝግጅት ላይ እንደሆነ ፓስተር ጻዲቁ ተናግረዋል።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት ፓስተር ጻዲቁ ከሲና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ ሰኔ 8 / 2017 ዓ.ም ከአንድ ዓመት በፊት ተመርቆ ለንባብ የበቃው መጽሀፍ በአሁኑ ሰዓት ለብዙዎች እንዲደርስ በአፋን ኦሮምኛ እና በትግረኛ እየተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።

በሙሉ ጊዜ አገልጋይነት ከ50 አመት በላይ ያገለገሉ #እና የሙሉ #ወንጌል ሴሚናሪን 9 ዓመታት የሙሉ ወንጌልን ቤተክርስቲያንን ደግሞ በዋና ጸሐፊነት 8 አመታት የመሩ እና በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት የሆኑት ፓስተር ጻዲቁ አብዱ ይህ መጽሀፍ ከ17 ዓመት በላይ ያስተማሩትን ትምህርት ወደ መጽሀፍ የተቀየረ ነው።

#ትንቢተ አብድዩ መጽሃፍ ላይ ተንተርሶ በመንታ ወንድማማቾ ስር በሰደደ ጸብ ምክንያት አንዱ ሞተ አንዱ ተሰደደ በትውልዳቸው ጥላቻ ስር ሰደደ። ይህን #ድንቅ ታሪክ ለሁሉም ሊሆን በሚችል መልክ ተርከውታል።

ሙሉ ቃለ መጠይቁን ለመመልከት ሊንኩን ይጠቀሙ https://www.youtube.com/watch?v=sU79nt70EYg&t=2463s
❤9👍1🔥1👏1🙏1👌1
August 12, 2026 1.2K