The Christian News: post #4703 — TG.ME

"እነዚህ 50 ዓመታት የሙላት፣ የሙቀትና የምቾት ዓመታት ብቻ አልነበሩም" ፓስተር ታምራት ሀይሌ

በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የዝማሬ አገልግሎት ብዙዎችን የባረኩት እና ከአንጋፋ አገልጋዮች መካከል አንዱ የሆኑት ፓስተር ታምራት ከሰሞኑ በካናዳ ስለተደረገላቸው ድንገተኛ ሰርፕራይዝ ምስጋናቸው አቅርበዋል።

በማህበራዊ ድህረገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የመላ ካናዳ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት "ለኅብረት ተጠርተናል" በሚል በቶሮንቶ ከተማ ባዘጋጁት በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ታላቅ ኮንፈረንስ ላይ እንድናገለግል በተጠራንበት፣ በኮንፈረንሱ መጨረሻ ላይ "የአገልግሎትህን 50ኛ ዓመት" በሚል በድንገት ሰርፕራይዝ አደረጉን።

"ብርሃነ ወንጌል" በተሰኘች ቤተክርስቲያን በመዘምራን ቡድን የተሰለፍኩበት ዓመት ተጨምሮ ሲሰላ በእርግጥም 50 ዓመት መሙላቱን ያስተዋልኩት በኋላ ነው። እነዚህ 50 ዓመታት የሙላት፣ የሙቀትና የምቾት ዓመታት ብቻ አልነበሩም። የምንኖርባት ምድር ጠፍጣፋ (Flat) ብቻ ሳትሆን ወጣገባ እንደሆነች ሁሉ፣ ሕይወትም እንዲሁ ውጣ ውረድ የበዛበት ቢሆንም ቅሉ፣ ጌታን ለመከተል የመጀመሪያዋን እርምጃ እግሬን ካንሳሁበት ዕለት ጀምሮ እስከዚህች ሰዓት ድረስ በማንከስም፣ በዳዴም ሆነ በሩጫ ዘመን እጄን ይዞ የመራኝን እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ፣ ይህን የሰማ ሁሉ ያመስግንልኝ።

ወንድሜ ሸዋዬ ዳምጤ እንዳዜመው፣ "ቀሪ ዘመኔን" እንዲባርክልኝ እለምነዋለሁ፣ እናንተም ለምኑልኝ።
"ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ፤ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው ለእግዚአብሔር መሠውያን አደርጋለሁ" (ዘፍ. 35:3) "አቤቱ አንተ ተስፋዬ ነህና፥ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ መታመኛዬ ነህና።

ተጨማሪ ለማንበብ Facebook
❤7👍4🔥1🥰1🙏1
August 8, 2026 1.1K 1 1