The Christian News: post #4702 — TG.ME

#የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን የወደፊት እጣ ፈንታ

#የቄስ ጉዲና ቱምሳ ሌጋሲ

የኢትዮጵያወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን የወደፊት እጣ ፈንታ እና የቄስ ጉዲና ቱምሳ ሌጋሲ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ።

“እነርሱም አንድ እንዲሆኑ” የሚለውን የዮሃንስ ወንጌል 17 መሰረት በማድረግ በአዲስ አበባ ቦሌ ኢላሜ ኮንቬንሽን ሴንተር በተካሄደው ፕሮግራም የቄስ ጉዲና ቱምሳን የአገልግሎት እና የህይወት ሌጋሲ ማውሳት እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን የወደፊት እጣ ፈንታ ዙሪያ ጽሁፎች ቀርበዋል ውይይት ተካሂዷል።

በመድረኩ የጉዲና ቱምሳ ፋውንዴሽን መስራች እና መሪ እንዲሁም የቄስ ጉዲና ልጅ ወ/ሮ ሌንሳ ጉዲና ተጋባዥ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ ሲሉ ተቀብለዋል። በመድረኩ ቄስ ዶ/ር ሳሙኤል ደረሳ፣ ዶ/ር ተካልኝ ነጋ እና ዶ/ር ለማ ደገፋ ጥናታዊ ጽሁፎች አቅርበዋል። ዶ/ር ምህረት ደበበ የእለቱ ተናጋሪ መልዕክት አስተላላፊ ነበሩ።

ቄስ ሃረገወይን ቃለ እግዚአብሔር ያቀረቡ ሲሆን፣ ቄስ ገመቺስ ደስታ (ፕሮፌሰር) እና ሃዋርያው ታምራት ታረቀኝ በጸሎት አገልግለዋል። ዘማሪ መስፍን ጉቱ፣ ዘማሪ ጳውሎስ ተገኝ፣ ዘማሪት ራሄል ተፈራ እና ዘማሪ ጉቱ ሽፈራው በዝማሬ ያገለገሉ ሲሆን የቢፍቱ ቦሌ መካነ ኢየሱስ ታዳጊዎች “አንድ ነን” የተስኘ ኬሮግራፊ አቅርበዋል።

በኦቦሌሳ አዶላ
❤5🔥2🥰2😭2👏1🙏1
August 7, 2026 1.1K 1