The Christian News: post #4698 — TG.ME

"ለአንድ ሀገር ዘላቂ መረጋጋትና ለጠንካራ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ መሠረት በሚሆኑ ዐበይት ጉዳዮች ላይ በሰለጠነ መንገድ ሐሳብ እየተለዋወጥን ነው" ፓስተር ጻዲቁ አብዶ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት ፓስተር ጻዲቁ አብዶ ከሰሞኑ እየተካሄደ ባለው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዙሪያ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው።

ፓስተር ጻዲቁ የምክክር ሂደቱ ልዩነቶችን በውይይት የመፍታት ባህልን የሚያጎለብትና ለትውልድ የሚሻገር ሰላምን የሚገነባ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ዋናው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በጉባኤው በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክሉ አራት ሺህ ተመካካሪዎች በመሰባሰብ በስምንት ዐበይት ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት እየተመካከሩ እንደሚገኙ የኢዜአ ዘገባ የሚጠቁም ሲሆን ኢዜአ ያነጋገራቸው ተመካካሪዎች፤ የምክክር ሂደቱ አሳታፊ፣ አካታችና ነፃ ሆኖ መካሄዱ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ ሀገራዊ መግባባትና ጠንካራ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ ተስፋ ሰጪ አዲስ ምዕራፍ መክፈቱን አክሎ ዘግቧል።
❤3🙏2👍1🔥1👏1
August 1, 2026 1.5K