The Christian News: post #4696 — TG.ME

ለአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ የሃይማኖት ተቋማት የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ጥሪ ቀረበ።

"አከባቢን መጠበቅ ፈጣሪን ማክበር ነው።" ሲሉ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጽሐፊ መጋቢ ታምራታ አበጋዝ የሃይማኖት መሪዎች፣ አገልጋዮች፣ ምዕመናን እና መላው የከተማችን ነዋሪዎች አከባቢ ጥበቃ የእያንዳንዱ ዜጋ እና የሃይማኖት ተቋማት የጋራ ኃላፊነት እንደመሆኑ መጠን እንዲሳተፉ ጥሪ አቀበዋል።

አካባቢያችንን መጠበቅ፣ የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን መንከባከብ እና ለመጪው ትውልድ አረንጓዴና ጤናማ አካባቢ ማስተላለፍ የሁላችንም የሞራልና የመንፈሳዊ ግዴታ ነው ያሉት መጋቢ ታምራት እንደ ሀገር በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን ጠቅሰው በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ/ም በአንድ ጀምበር አንድ ሚልዮን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት የተጠናቀቀ በመሆኑ በዚህ ታላቅ ሀገራዊና ከተማ አቀፍ ዘመቻ ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ምዕመናን በመርሀ ግብሩ በንቃት እንዲሳትፉ ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን ብለዋል።

እያንዳንዱ የሚተከሉ ችግኞች ለአረንጓዴ ኢትዮጵያ፣ ለንጹህ አየር፣ ለተሻለ አካባቢ እና ለዘላቂ ልማት የሚደረግ ዋጋ ያለው አስተዋፅኦ በመሆኑ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ አገልጋዮች ምዕመናንና ምዕመናት የአከባቢ ጥበቃን እንደ መንፈሳዊ ኃላፊነት በመቁጠር፣ በዚህ ታላቅ ሀገራዊ ከተማ አቀፍ ተግባር በንቃት እንዲሳተፉ በድጋሚ በጉባኤያችን ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን።

"ዛሬ የምንተክለው ችግኝ፣ ነገ ለልጆቻችን የምንሰጠው ተስፋ ነው።" እንተክል! እንጠብቅ! አረንጓዴ ኢትዮጵያን አዲስ አበባን በጋራ እንገንባ! ሲሉ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
❤9👍1🔥1👏1
August 1, 2026 1.3K