ጥቂት ስለ ግብፅ በጋዜጠኛ ዳንኤል መምሩ ፦ 📃የግብፅ እግርኳስ አመራሮች ከኮንጎ ጋር በሚደረገው ጨዋታ… — Sport News/ስፖርት ዜና — TG.ME

ጥቂት ስለ ግብፅ በጋዜጠኛ ዳንኤል መምሩ ፦

📃የግብፅ እግርኳስ አመራሮች ከኮንጎ ጋር በሚደረገው ጨዋታ መልካም እድል ይዞ ይመጣልናል በሚል በሬ አርደው መስዋዕት አቅርበው ነበር።

📃ጉዳዩ ከሁለት ቀናቶች በፊት ነበር የተሰማው። ግን መስዋዕቱ ተቀባይነት ያገኘ አልመሰለም ግብፅ ከአፍሪካ ዋንጫው ውጪ ሆናለች!

📃በእርግጥ ስጋው በግብፅ ለተቸገሩ ወገኖች እንዲከፋፈል ይደረጋል።

📃ግብፅ ከዚህ ቀደም በ 2008ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ተመሳሳይ የበሬ እርድ መስዋዕት አቅርባ ነበር። ታዲያ ያኔ የአፍሪካ ሻምፒዮን ሆነው ነበር። ትንሽ ቀየር ቢያረጓት አሪፍ ነበር😁

📃የቀድሞ የግብፅ ኮኮብ ሆሳም ሀሳን ሚዶ ፖሊሲያችንን በመቀየር አዲስ አቢዮት ማስነሳት አለብን ብሏል።

በመጨረሻም እቺን ለቅምሻ…

⚡️የአፍሪካ ዋንጫውን ብዙ ጊዜ ያሸነፈችው ግብፅ (7) ፣ ሁለተኛ አሸናፊዋ ካሜሩን (5) ፣ ሶስተኛ አሸናፊዋ ጋና (4)…ሁሉም ከአፍሪካ ዋንጫው በጊዜ ተሰናብተዋል!
❤5👍3🥰2
January 29, 2024 3.3K 2