ጉዞና ስንቅ ልጆችን ማሳደግ ትዕግስት፣ ዕውቀትንና ጥበብ የሚፈልግ በዋነኝነት ደግሞ የማያቋርጥ ዱዓን የሚጠይቅ ረጅም ጉዞ ነው። ቁርኣንና ሱንና ደግሞ በዚህ ጉዞ ላይ ብርሃን የሚሆኑን መመሪያዎቻችንና የጉዟችን ስንቅ ናቸው። የልጆቻችንን ልብ በእምነት እናንፀው! በተግባራችን አርአያ እንሁናቸው! በፍቅርና በእዝነት እንንከባከባቸው! በእጆቻችን የያዝናቸውን የአደራ ፍሬዎች በመልካም ተርቢያ እናስጊጣቸው። ከሁሉም በላይ ደግሞ፣ ጥረታችንን እንዲያሳምርልንና ልጆቻችንን ለኛ የዓይን ማረፊያ እንዲያደርግልን አላህን እንለምነው። "እነዚያም «ጌታችን ሆይ! ከሚስቶቻችንና ከዘሮቻችን ለዓይኖች መርጊያን ለእኛ ስጠን፡፡ አላህን ለሚፈሩትም መሪ አድርገን» የሚሉት ናቸው፡፡" (ሱረቱል ፉርቃን 25:74) #የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች #ምክር_ለተርቢያ 📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው! መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ! 💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫
June 8, 2025 201 1