ወርቃማዎቹን ቀናት በንቃት! ያለነው አላህ የመረጣቸው፣ ከሌሎች ቀናት ሁሉ በላይ ከፍ ያደረጋቸውና ወደር… — AYA Media || አያ ሚዲያ — TG.ME

ወርቃማዎቹን ቀናት በንቃት! ያለነው አላህ የመረጣቸው፣ ከሌሎች ቀናት ሁሉ በላይ ከፍ ያደረጋቸውና ወደር በሌላቸው የዙልሒጃ የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት ነው። በእነዚህ ቀናት ሚዛኖች ይለወጣሉ! ምንዳዎች ይነባበራሉ! አላህ በእነዚህ ቀናት ምሏል! "በንጋትም እምላለሁ፤ በአስር ሌሊቶችም፡፡" [አል-ፈጅር 1-2] እነዚህ አስር ቀናት እንደወትሮው ተራ ቀናት አይደሉም፤ ይልቁንም አላህ የወደዳቸው የባረካቸውና ምንዳዎች እጥፍ ድርብ የሚሆኑበትን እድል ያመቻቸበት ወርቃማ ቀናት ናቸው። ነቃ በልና ቅድሚያ የምትሰጣቸውን ጉዳዮች እንደ አዲስ አስተካክል። ከንቱ ወሬን ቀንስና አላህን ማውሳትን (ዚክርን) አብዛ። የስክሪን ጊዜህን አጥፋና የቁርኣንን ብርሃን አብራ። ጠዋትህን በተክቢራዎች ጀምር፤ ምሽትህን በዱዓዎች ደምድም። በእያንዳንዱ ቀንም ፈገግታ ወይም መልካም ቃል ቢሆን እንኳ ሶደቃ አድርግ። እነዚህ አስር ቀናት የሚባክኑበት ጊዜ አይደሉም፤ ይልቁንም ፍሬያማ የሚደረጉ ጊዜያት ናቸው። ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ “ከእነዚህ (የዙልሒጃ) አስሩ ቀናት የበለጠ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ የሆነባቸው ቀናት የሉም።” አላህ ያንቃን! #የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ 📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው! መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ! 💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫

May 31, 2025 216