በልጆች ልብ ውስጥ የአላህን ውዴታ ማስረፅ የሰው ልጅ ነፍስ መልካም ለዋለለት አካል ውዴታና ፍቅር እንዲኖረው… — AYA Media || አያ ሚዲያ — TG.ME

በልጆች ልብ ውስጥ የአላህን ውዴታ ማስረፅ የሰው ልጅ ነፍስ መልካም ለዋለለት አካል ውዴታና ፍቅር እንዲኖረው ሆኖ ተፈጥሯል። ልጆችም የዚህ ተፈጥሮ ድርሻ ተካፋይ እንደመሆናቸው መልካም ወደሚያደርግላቸው አካል በጣም የማዘንበል ባህሪ አላቸው። ታዲያ ልጆችን ከለጋ ዕድሜያቸው ጀምሮ  አላህ ስለዋለላቸው የተለያዩ ፀጋዎች በመዘርዘር የአላህን ውዴታ በልባቸው ውስጥ የማስረፅ ሥራ ይጠበቅብናል። ሁሉም ፀጋዎች ከአላህ የተሰጡን መሆናቸውና ማስረዳት ይኖርብናል። አላህ እንዲህ ብሏል፦ ﴿ وَمَا بِكُم مِّن نِعْمَةٍ فَمِنَ اللَّهِ ﴾ "ማንኛውም በእናንተ ላይ ያለው ፀጋ ከአላህ ነው፡፡" [አን-ነሕል ፡ 53] አላህ እንዲህ ብሏል፦ ﴿هُوَ الَّذِي خَلَقَ لَكُم مَّا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ﴾ "እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡" [አል-በቀራ ፡ 29] ስለዚህ ወላጆች ለልጆቻቸው የአላህን ፀጋዎች ያለማቋረጥ  መንገር ያስፈልጋቸዋል፤ ከእነዚህም መካከል፦ አላህ ነው የፈጠረን አላህ ነው የምናይባቸውን ዓይኖች የሰጠን አላህ ነው የምንሰማበትን ጆሮ የሰጠን አላህ ነው የምንበላባቸውን ጥርሶች የሰጠን አላህ ነው የምንራመድባቸውን እግሮች የሰጠን እንዲህ እያልን የአላህን ፀጋዎች እንቆጥራለን፤ ፀጋዎቹ ሊቆጠሩና ሊዘረዘሩ እንደማይችሉም እንነግራቸዋለን። ﴿ وَإِن تَعُدُّوا نِعْمَةَ اللَّهِ لَا تُحْصُوهَا ﴾ "የአላህንም ፀጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም።" [አን-ነሕል ፡ 18] #የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ 📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው! መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ! 💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫

May 30, 2025 204