እይታችሁን ጠብቁ — ኢማናችሁንም ጠብቁ! ከኢብራሂም ቢን አድሃም (አላህ ዘንላቸው) የተገኘ ዘመን ተሻጋሪ… — AYA Media || አያ ሚዲያ — TG.ME

📌 እይታችሁን ጠብቁ — ኢማናችሁንም ጠብቁ! ከኢብራሂም ቢን አድሃም (አላህ ዘንላቸው) የተገኘ ዘመን ተሻጋሪ ድንቅ ማስታወሻ "ሐሰትን አብዝቶ መመልከት የእውነትን ዕውቀትና ግንዛቤ ከቀልብ (ከልብ) ያስወግዳል።" 📖 ሒልየቱል-አውሊያእ (2/8) ዛሬ ላይ ማህበራዊ የትስስር ገጾች በሐሰት ተሞልተዋል፤ ነውር እየተፈላፈሉ መዘክዘክ፣ ሙዚቃ፣ ፊልም፣ ሐሜት፣ ብልግና እና ኢስላምን የሚቃወሙ አስተሳሰቦች እንደ አሸን ፈልተዋል። እኛም ሆነ ልጆቻችን እነዚህን ነገሮች ላይ ደጋግመን  ስናፈጥባቸው ጊዜያችንን ማባከን ብቻ ሳይሆን ቀልባችንን እየገደሉብን፤ ኃጢዓትና አመፆችን እንድንላመድ እያደረጉን ይገኛሉ። 🛑 አንድ ሰው ዓይኖቹን ለኃጢዓት ባጋለጠ ቁጥር ቀልቡ ከእውነት እየተጋረደና እየታወረ ይሄዳል። ምክርን መጥላት፣ ቁርኣንን መርሳት፣ ሱናን ማቃለል እና ከአላህ መራቅ ይጀምራል። እውነትን በእውነትነቱ መቀበል፤ ውሸትን በውሸትነቱ መራቅ እየተሳነው ይሄዳል! 🔒 ዓይኖቻችንን እንጠብቅ፤ የቀልቦቻችን በር ናቸውና። ዓይኖቻችንን፣ ጆሮዎቻችንና  ቀልቦቻችንን በቁርኣን፣ በሐዲስ እና በዚክር እንሙሏቸው ሕያው እናድርጋቸው። ያለ ዓላማ ለሚደረግ ስክሮሊንግ 'ይብቃ' በሉ።  ዓላማ ላለው ሕይወት 'ነቃ' በሉ። 📌 እይታችሁን ጠብቁ — ኢማናችሁንም ጠብቁ! #የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ 📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው! መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ! 💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫

May 29, 2025 224 1
እይታችሁን ጠብቁ — ኢማናችሁንም ጠብቁ! ከኢብራሂም ቢን አድሃም (አላህ ዘንላቸው) የተገኘ ዘመን ተሻጋሪ… — AYA Media || አያ ሚዲያ — TG.ME