እንቅፋት አይሁንባችሁ! ወላጆች ሆይ! ለልጆቻችሁ ያላችሁ ፍቅር፣ እዝነትና ርህራሄ ትለክክለኛውንና ቀጥተኛውን ጎዳና ለማመላከት እንቅፋት አይሁንባችሁ! ልጆቻችሁ ዛሬ በመልካም ስታዟቸው ከመጥፎ ስትከለሏቸው ልጅነት ይዟቸውና በህይወታቸው ጣልቃ የገባችሁ መስሏቸው ጥላቻ ቢያሳይዋችሁ ቢከፉባችሁም! ነገ እነርሱን ለማሳደግ ያያችሁትን ፍዳና መከራ፤ እነርሱን የተሻለ ሰው ለማድረግ የከፈላችሁትን ዋጋና ያደረጋችሁትን ጥረት በመረዳት ያመሰግኗችኋል! ነገ ደግሞ ሩቅ አይደለም! … የሚመጣ ነገር ሁሉ ቅርብ ነው! ለውድ ስጦታችሁ! ለመልካም ወላጅነታችሁ በዱኒያ ተንከባካቢያችሁ፤ ከህልፈት በኋላም በመልካም ዱዓቸው አስታዋሽ ይሆኗችኋል! ﴿ ... رَبَّنَا هَبْ لَنَا مِنْ أَزْوَاجِنَا وَذُرِّيَّاتِنَا قُرَّةَ أَعْيُنٍ وَاجْعَلْنَا لِلْمُتَّقِينَ إِمَامًا﴾ [ الفرقان: 74] #የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች #ምክር_ለተርቢያ 📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው! መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ! 💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫
May 20, 2025 234