🌅ኦርቶዶክሳዊ_የክርስትና_ሕይወት🌅: post #145 — TG.ME

#አምስተኛ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደግሞነበር ኒቆዲሞስ በመጀመር ላይ እንደ አንድ የእግዚአብሔር ነቢይ
የተመለከተው። "ከእግዚአብሔር ዘንድ
እንደመጣህ እናውቃለን "ሲልም ከእግዚአብሔር የተላከ ነቢይ ብቻ መስሎት ስለነበር ነው። ጌታችን
ግን ከሰማይ ተልኮ የመጣ መኾኑንና ነቢይ አለመኾኑን በኹሉም ቦታ ያለ መኾኑን በማብራራት አስተምሯል።
በመኾኑም #ኒቆዲሞስ_ኾይ_እኔ_እዚህም_እዛም_አለኹኝ_እንደነቢያት_የምላላክ_አይደለኹም_በሰማይም_ከሰማይም_በታች_አለኹኝ_ሲል_ነው። ይህ እንግዲህ የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋዌ የመለኮትን ምሉዕ በኩለሄ መኾን አለማስቀረቱን ያስገነዝበናል። አይሁድ ለከባድ ስሕተት የተጋለጡት ክርስቶስን ውስን አድርገው እንደራሳቸው በማየት ነው። የሚናገራቸው ንግግሮች ይገባቸዋል ነገር ግን አይቀበሉትም። እርሱ እናንተ ሥጋዬን ብቻ በማየታችሁ ምክንያት ተራ ዕሩቅ ብእሲ ነህ ትሉኛላችሁ እኔ ግን በሰማይም በምድርም የመላኹ ነኝ በማለት ከሰማይ ከወረደው በቀር በሰማይ የሚኖር ማንም የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው እንጂ በማለት በአንቀጸ ኒቆዲሞስ ለአይሁድ ያስረዳው።
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
@SPIRTUALITY @SPIRTUALITY
#ስድስተኛ_ከሰማይ_የወረደው_በራሱ_ፈቃድ_እንደኾነ_ወደ_ሰማይም_ያረገው_በራሱ_ፈቃድ_መኾኑን_ሲያስረዳ_ነው።
ሌሎች ቢያርጉ እግዚአብሔር ነው የሚያሳርጋቸው የሚወስዳቸው ርሱ ግን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ስለኾነ በራሱ ሥልጣን ነው ያረገው። ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም ማለት በሥልጣኑ ወረደ በሥልጣኑ ወጣ ማለት ነው። ለዚህ ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ድል መንሣት ባለበት የነጋሪት ድምፅ እግዚአብሔር ዐረገ አለ(መዝ 46፥5)፤ ርሱ ዐረገ አለ እንጂ መላእክት አሳረጉት አላለም፤ በፊቱ መንገድ የሚመራ አልፈለገም፤ በዚያው ጎዳና ርሱ ዐረገ እንጂ፤ ኤልያስ በዚያ መንገድ እንደ ክርስቶስ እንዲህ ሊያርግ አልቻለምና የኤልያስ ባሕርይ በዚኽ መንገድ ሊያርግ አልቻለም፤ መላእክት ወደ ታዘዙበት ቦታ ወሰዱት እንጂ(2ነገ 2፥11) አንድ አካል አንድ ባሕርይ የሚኾን የእግዚአብሔር ቃል መላእክትን የፈጠረ ነውና በሥልጣኑ ዐረገ፤ ስለዚህም ወንጌላዊው ሉቃስ የሐዋርያትን ሥራ በሚናገር መጽሐፍ ወደ ሰማይ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ርሱ አቅንተው ያዩ እንደነበር ተናገረ፤ አሳረጉት አላለም ወይም ተሸከሙት አላለም፤ ያረገበት ቦታ ገንዘቡ ነውና" ሃይ ዘቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ ምዕ 67 ክፍል 13 ቁጥር 12-15። ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግም የጌታን ዕርገት እንዲህ ይገልጽልናል "#በራሱ_ሥልጣን_ተነሣ_ርሱን_ያስነሣው_ማንም_አይደለም_በሚያርግም_ጊዜ_ማንም_ርሱን_ያሳረገ_አይደለም። ኤልያስን አስመልክቶ ዕርገቱ በጌታ አማካኝነት የኾነ ነውና እንዲያርግ ያደረገው ጌታ ነው፤ ከዚህም የተነሣ በሠረገላ እና በእሳት ፈረስ የከበረ ሥነ ሥርዐት ተደረገለት(2 ነገ2፥11)፣ ምክንያቱም ወደ ዐረገበት ቦታ በራሱ ማረግ አይቻለውምና፤ የጌታችን ግን እንደተጻፈ ተለየ፤ ወደ ላይ ለመነሣት ምንም ዐይነት መንኮራኩር አላስፈለገውም፤ በአንድ ቦታ በተወሰነ ጊዜ የሚቀመጡት ሰው በአጋዥ መውጣት ያስፈልገዋል፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ ብቻ ነውና፤ የእግዚአብሔር ልጅ ግን ራሱ እግዚአብሔር ነውና መንኮራኩር አያስፈልገውም "(ነገረ ክርስቶስ ገጽ 219-220)። በመኾኑም ጌታችን ከሰማይ በራሱ ሥልጣን
የተዋሐደውንም ሥጋ በራሱ ሥልጣን እንዳሳረገ የሚያስረዳ ንባብ ነው። ሰማያዊ ሥልጣን ያለው የሥልጣን ባለቤት መኾኑን ማቴ 10 ላይ ለዐሥራ እንደወረደኹለቱ ሐዋርያት ሙታንን የማስነሣት፣ ድዊያንን የመፈወስ፣ አጋንንትን የማስወጣት ሥልጣን እንደሰጣቸው ያስገነዝበናል። ያም ብቻ የቅድስት ሥላሴን ልጅነት የምናገኘው እርሱን አምላክ ነው ብለን ስንቀበለው በሚሰጠን ሥልጣን ነው። መጽሐፍ ለተቀበሉት ኹሉ ግን በስሙ ለሚያምኑ የእግዚአብሔር ልጆች ይኾኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው ተብሎ በዮሐ 1 ላይ ሳይኾንተጽፏል።
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
@SPIRTUALITY @SPIRTUALITY
#ሰባተኛ_ቅዱስ_አውግስጢኖስ_ደግሞ_ወደ_ሰማይ_የምንወጣበትን_መንገድ_ሊሰጠን_መውረዱንና_ወደ_ሰማይ_ይዞን_ወጥቶ_ደግሞ_የእግዚአብሔርን_ፈቃድ_የምናደርግበትን_ኃይል_ለእኛ_እንደሰጠን_ሲያስረዳ_ነው ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም የተባለው። ከሰማይ ከወረደው ሲል መንገዱን እንደሰጠን፤ ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም ሲል የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንረዳበትን ኃይል እንደሰጠን የሚያስረዳ ነው።

#በኢየሱስ_ክርስቶስ_አምላክነት_ሥጋዌ_ስናምን_የሰማዩን_የእግዚአብሔርን_ፈቃድ_የምንረዳበትን_ጥበብ_ኃይል_እናገኛለን_ሲል_ነው። እንግዲህ መንገዷ ማለት እውነተኛይቱ ሃይማኖት ናት፤ነብዩ ሆሴዕ የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ናት ጻድቃን ይሔዱባታል ኃጥአን ግን ይወድቁባታል በማለት የገለጸልን ንጽሕት መንገዳች አንዲቷ ሃይማኖታችን ናት። በዚህች ርትእት መንገድ ስንጓዝ ፈጻሚያነ ፈቃደ እግዚአብሔር ወደ መኾን እንሸጋገራለን።
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
@SPIRTUALITY @SPIRTUALITY
ስምንተኛ አኹንም ቅዱስ አውግስጢኖስ እንዲህ ይላል። #ባል_እናትና_አባቱን_ይተዋል_ከሚስቱም_ጋር_አንድ_ይኾናል_እንደተባለ_የቤተክርስቲያን_ሙሽራ_ክርስቶስም_አብን_አባቱን_ትቶ_ሲባል_ቅዱስ_ጻውሎስ_እንዳለው "እርሱ የእግዚአብሔር መልኩ ነው ቀምቶ እግዚአብሔር የኾነ አይደለም። ነገርግን የባሪያውን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ኾኖ ራሱን ዝቅ አደረገ። ፊል 2፥7 በሚለው ነው። #እናቱን_ትቶ_ሲል_ከእናቱ_መወለዱን_ሲል_ነው_ከሚስቱ_ማለትም_ከሙሽሪት_ቤተክርስቲያን_ጋር_አንድ_ኾነ_ማለት_ነው።
በዚህም ምክንያት ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም ሲል፦ ከሰማይ ከወረደው ጋር አንድ አካል ያልኾነ ወይም ከሰማይ የወረደው ያላደረበት ማንም ወደ ሰማይ ሊወጣ አይችልም። ከሰማይ በወረደው በእግዚአብሔር አሳራጊነት ካልኾነ በቀር ማንም ሊያርግ አይችልም። ይህ የሚያሳየው አንድነትን ነው። ቤተክርስቲያንን ያለ ክርስቶስ ማረግ አትችልም ሲል ነው። ክርስቶስ የቤተክርስቲያን ራስ ሲኾን ቤተክርስቲያን ደግሞ አካሉ ናትና የቅዱሳን ኹሉ ዕርገት በባላቸው በክርስቶስ ወይም በራሳቸው
በክርስቶስ የሚኾንና ርሱም አንድ መኾኑን የሚያስረዳ ነው። ስለዚህ ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጎምደው ራሳቸውን በነፍስ በሽታ ውስጥ እንደከተቱት መናፍቃን ሳይኾን በቅድስናና በንጽህና አጥርነት ራሳቸውን ጠብቀው በእግዚአብሔር መንፈስ በተረዱት በአባቶቻችን ትርጓሜ መሠረት የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር እንድንጠጣ እግዚአብሔር ይርዳን አሜን።

@SPIRTUALITY @SPIRTUALITY
❖ወስብሐት ለእግዚአብሔር!❖
በዲ/ን ዮሐንስ
June 8, 2019 5.6K 24