Samuel Belayneh Qaa'me: post #648 — TG.ME

ሰለፍትህ ስትጮህ “ሰብዓዊ” ይሉሃል።
ምርትና አገልግሎታቸውን፣ ወይም የእነሱ የሆነውን ነገር ስታስተዋውቅ “ምርጥ ሰው!” ይሉሃል።
የወንጌል አማኝ ሆነህ ሳለህ ሁሉንም ሐይማኖት የሚያማክል የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ስትተገብር “ሚዛናዊ” ይሉሃል።
የራህን ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ማንነት ትተህ ሰለ ከተሜው ስታወራ “ምርጥ ኢትዮጵያዊ” ይሉሃል። በአንዳች አጋጣሚ ተሳስተህ እንኳን ሰለህዝብህ ጥቅም ከተናገርክ “ዘረኛ!” ይሉሃል። 😏 ሰለ ህዝቤ መብትና ጥቅም በተናገርኩት ካሉኝ ዘረኛ፣ ይበሉኛ።🎯

አቶ ሳሙኤል በላይነህ ቃ'ሜ ሀገሩን ይወዳል። የሌሎችን መብትና ጥቅም ማክበር ያደግበት የአባቶቹ ባህርይ ነው። ያስቀጥለዋል። በሰፊው የሲዳማ ህዝብ ጥቅም በፍፁም አይደራደርም። በዚህ በአጭር ዕድሜዬ የተረዳሁት ነገር ቢኖር ሰለ ህዝብህ ስትናገር "ዘረኛ" ከሚሉቱ በለይ በኢትዮጵያ ምድር ዘረኛ አለመኖሩን ነው። ሲዳማነቴን ካልተቀበልክ ከአንተ ጋር የሚጋራው ኢትዮጵያዊነት ያው ፌክ ነው!! በሃላሌ (በእውነት) እንገዛለን። ዛቻ፣ ስድብ፣ ዘመቻ ፈርተን ግን ህሊናችን እያወቀ የምሸቅጠው የህዝባችን ጥቅም አይኖርም።
❤65👍10
January 14, 2026 3.7K