Bocaasa 10, Wolaphote Barra | ህዳር 10🎯
በሐዋሳ ከተማ የሲዳማን ሕዝብ ታሪክ፣ ባህልና ማንነት የሚገልጹ ፕሮጀክቶች እንዳይገነቡ የተፈለገው ለምንድነው? ምንድነው እየታሰበ ያለው? ነገሮችን በጥርጣሬ ከማየት አንቧዝንም!!
🎯 የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ምልክት የሆነው የሻፌታ ታወር ግንባታ፣
🎯በአርበኞች ስም የሚሰየሙ ተቋማት፣ መንደሮች፣ መንገዶችና አደባባዮች፣
🎯የሲዳማን ህዝብ እሴት የሚመጥን በሐዋሳ ከተማ መሃል ትልቅ ሙዚየም ግንባታ፣
🎯የሎቄ ሰማዕታት ሃውልት፣
🎯የየአፊኒ አደራሽ
🎯የሰማዕታት ፓርክ ግንባታ ወዘተ የሲዳማን ህዝብ ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነት የሚገልጹ በመሆናቸው ሆን ተብለው በሸፍጥና በሴራ የተጓተቱ ይመስለኛል።
የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ በእሳቸው አስተዳደር ዘመን ተጀምሮ ቆሞ የቀረውንና ሦስት ከንቲባዎች የተፈራረቁበትን የሻፌታ ታወር ፕሮጀክት በፍጥነት አስጀምሮ ያስጨርሰዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።
በግሌ በብልፅግና መንግሥት ላይ ያለኝ እምነት የሚጠነክረው ከምንም በላይ ህዝቤን የሚገልጽ ምልክት በሐዋሳ ከተማ በስፋት ማየት ስችል ነው።
ሳሙኤል በላይነህ ቃ'ሜ (ሳበቃ)
ሕዳር 10, 2018 ዓ.ም
ሐዋሳ፣ሲዳማ | ኢትዮጵያ 🇪🇹

56
13
1November 19, 2025 4.1K 3