የምክንያታዊ ባለራዕዎች ስብስብ (RVC): post #2364 — TG.ME

ሳይኮ-አናሊስስ

"የቴራፒ ውይይትና ህክምና-ህልምን ለህክምናው ጠቃሚ በሆነ መልኩ ለመፍታት፤ንቁ ከሆነው የህሊና ክፍል የተሰወሩ ስሜቶችን፥ፍርሀቶችን፥ፍላጎቶችን ለማወቅ፤ማወቁ ደግሞ ከጭንቀት እና ከድብርት ብሎም ማንነትን ካለመቀበልና ከእብደት እንዲጠብቀን-የሚደረግ ነው።"

ጥያቄው
፩.ሰው ከስነ-ልቦናዊ እውነቱ ጋር መኖር ይችላል?
(Werner Herzog: የቤቱ እያንዳንዱ ጨለማ ክፍል ላይ ማብራት ክፍሉን ምቾት የለሽና የማይለመድ ያደርገዋል።)
"ENERGY DISSIPATION፡በአጽናፈ-አለም ውስጥ ያለ ጉልበት ወደ ሌላ ገፅታ(ፎርም) ራሱን ከመቀየሩ በፊት ሊጠፋ እና ጠፍቶ ሊቀር ይችላል።"

፪.ትውስታ ውስጥ ሁሉንም እውነት ፈልጎ ለማግኘት መሞከር ትክክለኛ አካሄድ ነው? ጠፍቶስ ሊቀር የሚችል የልጅነት እና የወጣትነት እውነት የለም?
"ህሊና ጥልቅ ነው እንበል፤በጥልቁ ውስጥ የሚያበሩ ክዋክብቶች አለፍ አለፍ ብለው ተበትነዋል። ግርዶሽ ብርሃን ስለመኖሩ የሚነግረን እውነት እንጂ በራሱ ተፈጥሮ አይደለም።"

፫.ንቁ ባልሆነው የህሊና ክፍል ውስጥ ጥላ እንጂ ሌላ ምን ሊኖር ይችላል?

📍🗺️ አድራሻችን RVC Telegram channel የቴሌግራም ቻናላችንን ላልተቀላቀላቹ ከታች ባለው ሊንክ መቀላቀል እንዳይረሳ።


#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
@RvcClub
@RvcClub
❤4
July 31, 2026 748 5