R e a l N o r t h™ 🧭: post #912 — TG.ME

✞ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን :- የሜኖናዊት /Anabaptist አስተምህሮ ተከታይ ናት። ➥ ጥምቀት:- የአዋቂ ጥምቀት ይህም ለቤተ ክርስቲያንና ለክርስቶስ የሚገባ ቃል ኪዳን ተደርጎ ይታያል። ➥ የጌታ እራት:- የአማኞች እኩልነትና የፍቅር ኅብረት መግለጫ ነው። ➥ አስተምህሮ:- ሰላማዊነት፤ ደቀመዝሙርነት እና የእግር ማጠብ ሥርዓት ልዩ መለያዎቿ ናቸው። ✞ የኢትዮጵያ ገነት ቤተ ክርስቲያን :- በፊንላንድ ሚስዮን አማካኝነት የተመሰረተች  የጴንጤቆስጤ Pentecostal አስተምህሮን የምትከተል ናት። ➥ ጥምቀት:- የአዋቂ የአማኝ ጥምቀት ብቻ በውኃ ውስጥ በመጥለቅ። ➥ የጌታ እራት:- የጌታ ሞትና ትንሳኤ መታሰቢያ ነው። ➥ ልዩ አስተምህሮ :- በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ልሳን፣ ትንቢት ታምናለች።    ከሌሎቹ ለየት የሚያደርጋት በአስተዳደር ረገድ "ኤጲስ ቆጶሳዊ" Episcopal መዋቅርን ትከተላለች፤ ማለትም የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ኤጲስ ቆጶስ" ተበለው ይጠራሉ። @Real_North

July 20, 2026 161 1