ነጠብጣብ...: post #625 — TG.ME

ሁሉንም ሰው ማስደሰት አትችልም


➡️ ብትወፍር ሆዳም ነው ትባላለህ

➡️ ክብደት ብትቀንስ ታሞ ነው ይሉሃል

➡️ ፏ ብለህ ብትለብስ ጉረኛ ትባላለህ

➡️ ቀለል አድርገህ ስትለብስ ደሃ ነው ይሉሃል

➡️ ቁምነገረኛ ብትሆን አሰልቺ ሰው ነው ይሉሃል

➡️ ቀልደኛ ስትሆን ያልበሰለ፣ህፃን ተብለህ ትታማለህ

➡️ በራስህ መንገድ መኖር ስትጀምር ሰው የማይወድ ትባላለህ

➡️ ለብቻህ ብትኖር ሲንግል ሆኖ ነው ይሉሃል

➡️ ስኬታማ ስትሆን አጭበርብሮ ነው ብለው ስምህን ያጠለሹታል

➡️ ሕይወትን ለመርታት ስትውተረተር ሰነፍ ትባላለህ

➡️ ለሰዎች መልካም  ስትውል ሞኝ ነው ብለው ያወሩብሃል

➡️ ማስመሰል ስታቆም ዘመድ አይወድም ይሉካል

➡️ Sport ስትሰራ ካዩህ ሴት ለማማለል ነው ይላሉ

➡️ ለሴት ክብር ስትሰጥ ካዩ ሴት አሽኮርማሚ ኮርማ ነው ይላሉ

➡️ ጓደኛህን ስትጋብዝ ካዩ ብሩን ለባዳ በታኝ ትባላለህ

ወዳጄ ሰዎች ምንም ብታደርግላቸው የሚሉት አያጡም። አንተ ብቻ የራስህን ቀለም ይዘህ ተራመድ። በየመንገዱ ዳር የሚያደናቅፉህን ጉቶዎች ባላዬ እለፋቸው። ጮኸው ሲታክታቸው በራሳቸው ድርጊት አፍረው ከስርህ መርመጥመጥ ይጀምራሉ። ውሾች ይጮሃሉ ግመሎች  ይሄዳሉ🙌

        t.me/Netebtab99
👍7❤1💯1
February 14, 2025 1.1K 4