ነጠብጣብ...: post #613 — TG.ME

ሕይወት በለውጥ እንጂ በዕድል አትሻሻልም። ሰው የምሩን ካሰበ ተዓምረኛ አልያም ሰበበኛ መሆን ይችላል ይላሉ የስነልቦና ምሁራን። በርካታ ወጣቶች ካሉበት ሁኔታ የተሻለ ነገርን ለምን አላስመዘገባችሁም ሲባሉ ዕድሉን ስላላገኘሁ ይላሉ። (በእርግጥ ለውጥን የሚፈጥረው እድል ነው)። ለለውጥ ያልተዘጋጀ ሰው ግን ምንም ያክል ዕድል ቢሰጠው ዕድል ሰጪውን ያማርራል እንጂ አንዳች ነገርን አይፈጥርም።

የሀብታም ልጅ ስለሆንክ ጥፋትም ልማትም ዕድልህ ነው። የምሁር ልጅ ስለ ሆንክ ለማወቅም ለተራ ሰውነትም ዕድሉ አለህ። የመሪ ልጅ ስለ ሆንክ መምራት አልያም መመራት ዕድልህ ነው። ራስህን ለማሻሻል ለለውጥ መሻት ወሳኝ ነው። ምርጫህን በትኩረት ተመልክተህ ፈቃድህን ተጠቅመህ ራስህን ለለውጥ ካላዘጋጀህና በመንገዱ ካልተገኘህ ሕይወት በዕድል ብቻ አትቃናም። ዕድል ሕይወትን ታሻሻል ዘንድ ለጥቂቶች የምትሰጥ ቢሆንም ለውጥ ግን ለአጠቃላይ የሰው ልጅ የተሰጠ እኩል የመሆኛ ክፍት መንገድ ነው።
      ካነበብኩት 📖

          t.me/Netebtab99
❤7👍3
December 22, 2024 762 3