Tiktok scroll እያደረኩ ነው። ጓደኛዬ ነው። ጥሩ ጥሩ content ይሠራል። አንዳንዴም የሚያስተምሩ፣… — NK's Journal — TG.ME

Tiktok scroll እያደረኩ ነው። ጓደኛዬ ነው። ጥሩ ጥሩ content ይሠራል። አንዳንዴም የሚያስተምሩ፣ አንዳንዴ ደግሞ የሚያዝናኑ ነገሮችን ነው የሚለጥፈው። ልክ ቪድዮው ሲመጣልኝ ምንም ሳልሰማ scroll up አደረኩ። ከዚያ ከስር ደግሞ የማላውቀውን ሰው video ተመስጬ ማየት ጀመርኩ። ከዚያ ግን እሱን እያዬሁ ቅር ቅር አለኝ። ስላሳለፍኩት ቪድዬ ማሰብ ተያያዝኩ። በቅፅበት ተሰማኝ። ለምንድነው አሁን scroll ያደረኩት? ቪድዮውን ሰምቼው ስላልተመቸኝ? ወይስ ጓደኛዬ ስለሆነ ምንም አዲስ ነገር አይፈጥርም ብዬ ስላሰብኩ? ወይስ ብዙ ጊዜ ስለማወራሁ ለምጄው ነው? እሱን ነበር ሳስብ የነበረው። ከዚያ ወዲያው ተመልሼ የጓደኛዬን ቪድዮ አይቼለት። React አድርጌ። በComment engage አድርጌ ምናምን አሳለፍኩ። እንዳጋጣሚ ደግሞ በጣም funny ነገር ነበር። ሳኩለት😁! ...በእጅ ያለ ወርቅ እንደመዳብ ይቆጠራል እንዲሉ የጓደኛችንን ሥራ ሳናበረታታ የማናውቀውን ሰው ስራ ስናሞጋግስ፣ ስንዘፍንለት እንውላለን። በtiktok ቋንቋ ደግሞ repost እና copy link share እናደርጋለን ማለት ነው። ጎበዝ Noooo! የጓደኛችሁን ምርት ተጠቀሙ። ግዙ። አበረታቱ። ለሌሎች አካፍሉአቸው። እኛው በእኛው ካልተረዳዳን ሌላ ማንም ሊረዳን የሚችል የለም። @nks_journal

August 23, 2026 610