Now I know the reason why የሸገር ልጆች don't take pictures on the… — NK's Journal — TG.ME

Now I know the reason why የሸገር ልጆች don't take pictures on the corridor ልማትs.

ፒያሳ ፋውንተኖች እና የተሰሩት ቆንጆ ቆንጆ ቦታዎች ላይ አንድም የአዲስ አበባ ልጅ excited ሆኖ ፎቶ ሲነሳ አታይም።

ብዙ ጊዜ በፒያሳ ሳልፍ ብዙ ሰዎች ተሰብስበው ግማሹ በጀማ፣ አሊያም በቤተሰብ፣ በትምህርት ቤት ምናምን መጥተው እየጎበኙ ፎቶ ለጉድ ሲነሱ አያለሁ። በእርግጠኝነት ደግሞ የሸገር ሲቲ ልጆች እንጂ የሸገር ልጆች እንዳልሆኑ የሚያሳብቁ😁 ብዙ ነገሮች አሉአቸው starting from their  pose😆

እና በቅርቡ የሆነች ከተማ ሄጄ ነበር። ላስካ የምትባል። እና እነሱም የሆነ corridor ልማት ብለው I  Laska የሚል በትልቁ ያለው  ነገር ሰርተዋል።

እና እሱጋ ሄጄ አንዴ ልብ ቅርፁጋ አንዴ ደግሞ ከፅሁፎቹ መሃል እየተዟዟርኩ ፎቶ  እየተነሳሁ ሳገኝ ነው ይኼ ነገር ትዝ ያለኝ።😆 ለእኔ ድጋሚ እዚያ ከተማ ላልሄድ ስለምችል ለማስታወሻ መሆኑ ነው። ከዚያ የከተማይቱ ሰዎች አፍጥጠው ያዩኛል እምቡር እምቡር እያልኩ ፎቶ ስነሳ።

ከዚያ መጣልኛ የፒያሳው ነገር። ለካ የፒያሳን ፏፏቴና ፋውንቴን enjoy እያደረጉ የነበሩት እንደእኔው የገጠር ሰዎች እንጂ ያን በየቀኑ ሲያዩት የነበሩት ሰዎች አይደሉም።

እኔ I thought በቃ የአዲሳባ ሰው ሥራ የፈታ። እና ምን ልበል? በየቦታው ተቆልለው ሲቀመጡ፣ አንዴ ደግሞ ሲሯሯጡ፣ አንዴ ደግሞ funny poses ምናምን እያሳዩ ሲነሱ 😆

ለካ የሸገር ሲቲ ሰዎች ነበሩ😆

@NKs_Journal
😁18🤣5❤4🤨1😡1
August 20, 2026 798 1 5