ተማሪ ካሊድ በሽር ከስድስት መቶ 591 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ተማሪ ሆነ!
በ2017 ዓ.ል የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 8.4 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ አምጥተዋል ብለዋል ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፡፡
585 ሺህ 882 ተማሪዎች ፈተናውን መፈተናቸውንም አንስተዋል፡፡ፈተናውን ከወሰዱ 48,929 ተማሪዎች አልፈዋል።
በ2017 ዓ.ሌ ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 8.4 ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ የትምህርት ዘመኑን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን አስመልክተው መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ካስመዘገቡት መካከል የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች 5.2 በመቶ፣ ተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ደግሞ 11.4 በመቶ የ እንደሆኑ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቅሰዋል፡፡
ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡም በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 ፦ 591 ወንድ (ተማሪ ካሊድ በሽር) ከዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት፤ 579 ሴት ተማሪ ከብስራተ ገብርኤል ትምህርት ቤት ሲሆኑ
በማህበራዊ ሳይንስ ፦562 ወንድ ከአምቦ ቦርዲግ ትምህርት ቤት ፤ 548 ከሴት ከሴንት ጆሴፍ ትምህርት መሆናቸውን ጠቅሰዋል በመግለጫቸው፡፡
በ2017 ዓ.ል የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 1 ሺህ 249 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ የ2017 ዓ.ል የትምህርት ዘመን ማጠናቀቂያን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት 50 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን አሳልፈዋል።
Munib_net

17
7
4
3
2
1September 15, 2025 6K 1