Mind Game Question | የጭንቅላት ጨዋታ ጥያቄ: post #328 — TG.ME

ይህንን ያውቃሉ⁉️

- ​በህንድ አንዳንድ ገጠር መንደሮች ውስጥ ዝናብ ሲጠፋና ድርቅ ሲከሰት "የእንቁራሪቶች ሰርግ" (Mandooka Parinaya) የማዘጋጀት እጅግ እንግዳ ባህል ያለ ሲሆን የአካባቢው ህዝብ እንቁራሪቶች የሚጮኹት ዝናብ እንዲዘንብ ለዝናብ አምላክ አቤቱታ ለማቅረብ ነው ብለው ስለሚያምኑ ሁለት ወንድና ሴት እንቁራሪቶችን በመያዝ ልክ እንደ ሰው ባህላዊ የሰርግ ልብስ አልብሰው በመቶዎች የሚቆጠሩ መንደርተኞች በተሰበሰቡበት በሙዚቃና በጭፈራ በድምቀት ያጋቧቸዋል 😁

- ... የሚገርመው ግን ሰርጉ ካለቀ በኋላ ሙሽሮቹ እንቁራሪቶች አብረው እንዲኖሩ "በጫጉላ ሽርሽር" መልክ ወደ አንድ ኩሬ በጋራ የሚለቀቁ ሲሆን ይበልጥ የሚያስቀው ደግሞ

- በአንድ ወቅት ዝናቡ ከልክ በላይ በዝቶ ጎርፍ ሊያስከትል ሲል፣ መንደርተኞቹ ዝናቡን ለማስቆም ሲሉ የተጋቡትን እንቁራሪቶች በይፋ "እንዲፋቱ" አድርነው ነበር 😂🐸💒

@mind_game_question
😁4❤1
May 30, 2026 387 1