ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች (ASTU & AASTU) የ2019 ዓ.ም የመግቢያ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ!
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች በኦንላይን የተመዘገባችሁ አመልካቾች በሙሉ
📅 የፈተና ቀን: ጳጉሜ 4 ቀን 2018 ዓ.ም
በዕለቱ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ ፈተናውን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ጠቃሚ ማሳሰቢያዎችና የፈተና መመሪያዎች
✓ ተፈታኞች በእለቱ ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ በመፈተኛ ጣቢያዎች በአካል በመገኘት ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባቸባቸዋል።
✓ ፈተናው የሚሰጥባቸው የትምህርት አይነቶች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብ እና እንግሊዝኛ ይሸፍናሉ።
✓ አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ፦
o የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት
o የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ)
o የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይኖርባቸዋል።
የተከለከሉ ነገሮች፡
✓በፈተናው ዕለት የሞባይል ስልኮችን እና ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ይዞ ወደ ፈተና ጣቢያ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
• ዲሲፕሊን፡ በፈተና ወቅት ማንኛውንም ያልተገባ ተግባር መፈፀም በጥብቅ የተከለከለ ነው።
ልዩ ማስታወሻ፡ የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሚደረገው መደበኛ የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም።
September 4, 2026 172

