የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ እንደምን አላችሁ ምዝገባ… — MatricET — TG.ME

MatricETPhoto
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ

እንደምን አላችሁ ምዝገባ በቅርቡ ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም የሚደረግ ሲሆን በሚከተሉት የትምህርት መስኮች በሁለቱ ዩኒቨርስቲዎች መካከል ይደረጋል።

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
ኢንጂነሪንግ
(ASTU)

Engineering Majors

👉🏽 አርክቴክቸር
👉🏽 ሲቪል ኢንጂነሪንግ
👉🏽 ወተር ሪሶርስ ኢንጂነሪንግ
👉🏽 ኬሚካል ኢንጂነሪንግ
👉🏽 ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
👉🏽 ማቴሪያል ሳይንስና ኢንጂነሪንግ
👉🏽 ኤሌክትሪካል ፓወር እና ኮንትሮል ኢንጂነሪንግ
👉🏽 ኤሌክትሮኒክስ እና ኮሚኒኬሽን ኢንጂነሪንግ
👉🏽 ኮምፒዩተር ሳይንስና ኢንጂነሪንግ 
👉🏽 ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ

Applied Science

👉🏽 አፕላይድ ባዮሎጂ
👉🏽 አፕላይድ ኬሚስትሪ
👉🏽 ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ
👉🏽 ፋርማሲ
👉🏽 አፕላይድ ፊዚክስ
👉🏽 አፕላይድ ጂኦሎጂ
👉🏽 አፕላይድ ማቲማቲክስ 

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU)

Engineering Majors

👉🏽 አርክቴክቸር
👉🏽 ሲቪል ኢንጂነሪንግ
👉🏽 ኬሚካል ኢንጂነሪንግ
👉🏽 ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
👉🏽 ኤሌክትሪካል እና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ
👉🏽 ኤሌክትሮሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
👉🏽 ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ
👉🏽 ኢንቫይሮሜንታል ኢንጂነሪንግ

Applied Science

👉🏽 ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ
👉🏽 ፉድ ሳይንስና አፕላይድ ኒዩትሪሽን
👉🏽 ጂኦሎጂ
👉🏽 ባዮቴክኖሎጂ 

የምዝገባ ጊዜ፡-

ከነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሌሊቱ 6 ሰዓት ይሆናል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦

የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ https://stu.astu.edu.et   ወይም www.aastu.edu.et; www.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡

We will share you the links here As soon as possible we get it that is made only for the registration

ፈተናው የሚሰጥበት ቀን፡-

በድህረ ገፃችን የምዝገባው ቀን ካበቃበት በኋላ እናሳውቃለን ፡፡

ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፦

በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ

የፈተና ጣቢያዎቹ ያላቸው የመፈተኛ ቦታ ውስን በመሆኑ ይህንኑ አውቃችሁ ቅድሚያ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

በቂ አመላካቾች የሌሉባቸው የፈተና ጣቢያዎች በቅርበት ወደሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ሊታጠፉ እንደሚችሉ እናሳውቃለን፡፡

ለፈተና የሚቀርቡት የአመልካቾች ስም ዝርዝራቸው እና የፈተና ጣቢያዎች በሚከተሉት ድረ-ገፆች፡-  www.aastu.edu.et ; www.astu.edu.et  እንደአመቺነቱም በe-mail የሚገለፅ ይሆናል፡፡

አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፣ ማለትም (ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ይመከራል፡፡ (which is the same as ur University Entrance Exams)

ፈተና የሚሰጠው በቀጥታ (online) ስለሆነ አመልካቾች በፈተና ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል ግራ መጋባትን ለማስቀረት በምዝገባ ጊዜ ከመመዝገቢያ ፎርማቱ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ ይመከራል፡፡

አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሚደረገው የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም፡፡

በውጤታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከላይ በተጠቀሱት ድህረ-ገፆች ይገለፃል፡፡

በመስፈርቱ መሰረት ያልተመረጡ አመልካቾች ከዚህ በፊት እንደሚደረገው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ይሆናል፡፡

በፈተናው ዕለት ማንኛውንም የሞባይል ስልኮችን ይዞ ወደ ፈተና ጣቢያ መግባት የተከለከለ ነው፡፡

በፈተና ወቅት ያልተገባ ተግባር መፈፀም በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
August 30, 2026 110 1