እድገት ሁሌም የተስተካከለና ቀጥተኛ አይደለም
ብዙውን ጊዜ ስኬትን እንደ ቀጥተኛ መስመር አድርገን እናስበዋለን። ነገር ግን እውነታው እድገት ልክ እንደተያያዘና እንደተወሳሰበ የክር ኳስ ነው፤ የተለያዩ ተግዳሮቶች፣ ጥርጣሬዎች እና ያልተጠበቁ ክስተቶች የተሞላበት።
ሁለት እርምጃ ወደፊት እየሄድክ አንዱን ወደኋላ የምትመለስ ቢመስልህም፣ እየወደቅክ አይደለም፤ ይልቁንም እያደክ ነው።
ሂደቱ በተወሳሰበ ወይም በተዘበራረቀ ሁኔታ ውስጥ ሲሆን ማስታወስ ያለብህ 3 ነገሮች አሉ፡
የመጀመርያው ስህተቶች የተግባር ማሳያዎች ናቸው። ስህተት የማይሰሩ ሰዎች አዳዲስ ነገሮችን የማይሞክሩ ብቻ ናቸው።
ሁለተኛው እንቅፋቶች ሽንፈት ሳይሆኑ መረጃዎች ናቸው። እያንዳንዱ እንቅፋት ለቀጣይ ሙከራህ ምን ማስተካከል እንዳለብህ የሚነግርህ ግብረ-መልስ (feedback) ነው።
ሦስተኛው ምቾት እና እድገት አብረው ሊኖሩ አይችሉም። ከተለመደው አቅምህ በላይ የሆነ ነገር ሲያጋጥምህ፣ አቅምህን በንቃት እያሰፋህ መሆኑን ያሳያል።
ያንን የተወሳሰበ ሁኔታ አትፍራ፤ ምክንያቱም ትምህርት የሚገኘው በዚያው ሂደት ውስጥ ነው።

6
2August 1, 2026 1.3K 2