አካባቢህ አንተን ይቀርጽኃል
በመርዛማ አፈር ውስጥ ጤናማና በደንብ የሚያድግ ተክል ማሳደግ አይቻልም። ለአንተም አእምሮ ሁኔታው ተመሳሳይ ነው።
ኃይል (Energy) በቀላሉ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው የሚተላለፍ ነው። ብታስተውለውም ባታስተውለውም፣ በዙሪያህ ያሉ ሰዎች አመለካከት፣ ልማድ እና የአስተሳሰብ መንገድ ያለማቋረጥ በአንተ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። ስንፍና፣ ደስታ ፣ ሃዘን ፣ ሳቅ ፣ብርታት ፣ ጉብዝና እነዚህ ሁሉ ከአንድ ሰው ወደሌላኛው ሰው የሚጋቡ/የሚተላለፉ ተላላፊ ናቸው።
ዛሬውኑ በዙሪያህ ያሉትን ሰዎች ገምግም!
ያለማቋረጥ ከሚያማርሩ፣ ጊዜህን በከንቱ ከሚያስጠፉህ ፣ በአንተ ራዕይ ላይ ጥርጣሬ ከሚፈጥሩ ፣ ወደራሳቸው ዝቅተኛ የምቾት ቀጠና ደረጃ ከሚጎትቱህ እንዲሁም ጉልበትህን ከሚጨርሱ ሰዎች ተጠበቅ።
ሰበቦችን እንድትተው ከሚገፋፉህ፣ ስኬቶችህን ከሚያከብሩ እና ከፍ ያለ ግብ እንድታወጣ ከሚያነሳሱህ ሰዎች ጋር ተወዳጅ።
ትክክለኛው አካባቢ ጥሩ ስሜት እንዲሰማህ ብቻ አያደርግም፤ ይልቁንም የተደበቀ አቅምህን ወደሚታይ እድገት ይለውጠዋል።
አስታውስ! በአንድ ክፍል ውስጥ ሁልጊዜ አንተ ብቻ በጣም ብልህ እና ጠንካራ ሠራተኛ ከሆንክ፣ በተሳሳተ ክፍል ውስጥ ነህ ማለት ነው። እንድታድግ የሚያስገድዱህን ቦታዎች ፈልግ።

7
3July 31, 2026 1.1K