ትኩረት ከፍጥነት ይበልጣል የሌዘር ጨረር ብረትን የሚቆርጠው በፍጥነት ስለሚንቀሳቀስ ሳይሆን፣ መላ ኃይሉን… — Maroset SkillLab — TG.ME

ትኩረት ከፍጥነት ይበልጣል

የሌዘር ጨረር ብረትን የሚቆርጠው በፍጥነት ስለሚንቀሳቀስ ሳይሆን፣ መላ ኃይሉን በአንድ ነጥብ(ቦታ) ላይ ስለሚያተኩር ነው። በፍጥነት መሮጥ ላይ ብቻ ትኩረት በሚያደርግ ዓለም ውስጥ፣ ትኩረት ማድረግ ትልቅ ችሎታ ነው።

በአንድ ጊዜ ብዙ ነገሮችን መስራት ተረት ነው። አብዛኞቹ ሰዎች የሚወድቁት ችሎታ ስለሌላቸው አይደለም፤ የሚወድቁት ትኩረታቸው ወደ አስር የተለያዩ አቅጣጫዎች ስለሚበታተን ነው።

አስር ነገሮችን በግማሽ መንገድ ብቻ መስራት፣ መጨረሻ ላይ አስር ያልተጠናቀቁ ችግሮችን ብቻ ያስቀርልኃል። እውነተኛ እድገት የሚመጣው አንድን ነገር በጥልቀት እና በጽናት ስንሰራ ነው።

🚫 ሥራ በዝቶብህ መዋል ማለት ውጤታማ መሆን ማለት አይደለም

🚫 በፍጥነት መስራት ማለት ስኬታማ መሆን ማለት አይደለም

ጥልቅ ትኩረትን ለማዳበር የሚረዱ 2 ህጎች፡

1️⃣ አንድ ቅድሚያ የሚሰጠውን ጉዳይ ምረጥ፡ ዛሬ ቢጠናቀቅ ሌሎች ነገሮችን ሁሉ ቀላል የሚያደርገው ያ አንድ ተግባር ምንድን ነው?

2️⃣ ትኩረት የሚሰርቁ በይነመረባዊ ነገሮችን አስወግድ፡ ለ90 ደቂቃዎች ያህል ሥራ ላይ ስታተኩር ስልክህን  በሌላ ቤት( ክፍል) አስቀምጥ ወይም "አትረብሹኝ" (Do Not Disturb) የሚለውን አማራጭ አብራ።

አንድን ተግባር ሳትጨርስ በሌላኛው ተግባር ያለማቋረጥ ስትቀያይር፣ አእምሮህ "የመቀያየር ዋጋ" (switching tax) ይከፍላል፤ ይህም ምርጥ የሚባለውን ስራህን ከመስራትህ በፊት ጉልበትህን ያሟጥጠዋል።

አንድን ነገር በጥልቀት መስራት በዘርፉ ብቃትን ያጎናጽፋል። አስር ነገሮችን በግማሽ መንገድ መስራት ግን ለከፍተኛ ድካም እና ለስሜት መዛል (burnout) ይዳርጋል። ተጨማሪ ጊዜ አያስፈልግህም፤ የሚያስፈልግህ ጥልቅ ትኩረት ብቻ ነው።
❤9
July 30, 2026 942 1