"አሁን የመጀመር" አስተሳሰብ
ፍጹም የሆነ ጊዜ መጠበቅ ሙሉ አቅምህን እንዳትጠቀም የሚያግድህ ትልቁ እንቅፋት ነው።
እውነታው ግን ይህ ነው፡ ፍጹም የሆነ ጊዜ የሚባል ነገር የለም፤ ያለው "አሁን" ብቻ ነው። ታላቁ መጽሐፍም "የመዳን ቀን አሁን ነው" አይደል የሚለው?
ፍጹምነትን መሻት ስራን ወደፊት የማስተላለፍ ወይም የማዘግየት ሌላ ስም ብቻ ነው።
ለራሳችን እንዲህ እንላለን፡
🚫 "ተጨማሪ ጊዜ ሲኖረኝ እጀምራለሁ።"
🚫 "ብዙ ገንዘብ ሲኖረኝ እጀምራለሁ።"
🚫 "በሚቀጥለው ዓመት እጀምራለሁ።" ነገር ግን "የሚቀጥለው ዓመት" የሚባለው ነገር እርግጥ አይደለም። ማንኛውም የዘርፉ ባለሙያ፣ ስኬታማ ሥራ ፈጣሪ ወይም ታላቅ አርቲስት፤ በአንድ ወቅት ፍጹም ባልሆኑ መሳሪያዎች፣ ያልተሟላ እውቀት እና በርካታ ጥርጣሬዎች መጀመርን የመረጠ ጀማሪ ነበር።
ይህንን እሽክርክሪት ዛሬ እንዴት መስበር ይቻላል?
ሙሉውን ፕሮጀክት ዛሬውኑ ለመጨረስ አትሞክር። በአንድ ጊዜ አንድ እርምጃ ብቻ በመውሰድ ጀምር፡
📍መጽሐፍ መጻፍ ትፈልጋለህ? አንድ አንቀጽ በመፃፍ ጀምር።
📍የተስተካከለ ሰውነት ትፈልጋለህ? 5 ፑሽአፕ በመስራት ጀምር።
📍ንግድ መጀመር ትፈልጋለህ? ስለ ገበያው ጥናት በማድረግ እና መረጃ በመሰብሰብ ጀምር።
ባለህ ገንዘብ ፣
ባለህ ዕውቀት ፣
ባለ ጊዜ ፣
ባለህ ጉልበት ፣
ባለህ ግንኙነት ዛሬውኑ ጀምር ፥ ከትንሽ ተነስቶ ማደግን ተማር።
የስራ መነሳሳትና ፍጥነት የሚፈጠረው ስራውን ከጀመርክ በኋላ እንጂ ከመጀመርህ በፊት አይደለም።

8July 29, 2026 905